የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር አድገናል በማለት የምናቀርበው ሪፖርት ሁሉ ውሸት ነው አሉ
Video News:
http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded <
http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=B-qttD_Z4jA&list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn> &v=B-qttD_Z4jA&list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn
Secret Speech of Abdi Muhamed:
http://www.youtube.com/watch?v=PHBfS8-tluc <
http://www.youtube.com/watch?v=PHBfS8-tluc&list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&feature=player_embedded> &list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&feature=player_embedded#!
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
11.05.2013
ኢሳት ዜና:-ፕሬዚዳንቱ የካቢኔ አመራሮችን እና የሶህዴፓ ፓርቲ አባሎችን በመሰብሰብ እንደተናገሩት ክልሉ እንደ ለማ እንደ አደገ ተደርጎ ለመንግስት የሚቀርበው ሪፖርት ሁሉ ግምገማ ለማለፍ ተብሎ የሚቀርብ በውሸት የተሞላ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በስሜት ውስጥ ሆነው ባደረጉት ንግግር “ እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ሪፖርት እውነት ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደለንም፤ ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ ናቸው። ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት የተሞሉ ሪፖርቶች ናቸው የሚቀርቡት ” ብለዋል
ፕሬዚዳንቱ ” 10 ሚሊዮን እንስሶች ክትባት እንደተደረገላቸው ሪፖርት አድርገናል፤ ሪፖርቱ እውነት ስለመሆኑ እንኳ የግብርና ቢሮው ሃላፊው መማል ( ማረጋገጥ) አይችልም። እንኳንስ 10 ሚሊዮን 500 ሺ እንኳን ስለመከተቡ ምን ማረጋገጫ ይገኛል። ለመሆኑ ህዝቡ ይህ ሁሉ ሲከተብስ አያይም ወይ?” በማለት የሚቀርበው ሪፖርት በሙሉ ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ አብዲ ሬዲዮ አዲስ አበባና ሬዲዮ ፋና ስለሌሎች አካባቢዎች እየዘገቡ ስለ ኦጋዴን ችግር አለመዘገባቸውንም ኮንነዋል።
“አዲስ አበባና ሬዲዮ ፋና ስለሌሎች አካባቢዎች ይዘግባሉ ፣ ነገር ግን ስለዚህ ህዝብ ችግር መዘገብ ነበረባቸው። አይዘግቡም። ማን ነበር ቃለምልልስ መስጠት የነበረበት? የወረዳ እና ዞን ሀላፊዎች ነበሩ።
አቶ አብዲ ” በክልላቸው ያሉ ባለስልጣናት በሰላም ገብተው በሰላም ማደራቸውንም እንኳ ለመንግስት ሪፖርት እንደማያደርጉ ገልጸዋል።
ኢሳት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የደረጉትን ሚስጢራዊ ንግግሮች ባቀረበው የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቱ ” ትግሬዎች፣ አማራ መልሶ ስልጣን እንዳይዝ ኦጋዴኖችን አስታጥቀው በጋራ አገሪቱን እንድንመራ ይፈልጉ ነበር፣ እኛ ግን እንደ አማራ ቆጥረናቸው ተኩስ ከፈትንባቸው፤ አማራ እና ትግሬ፣ አማራ እና ኦሮሞ መቼውንም አይታረቁም ፣ አይተባበሩም ስለዚህ የኦጋዴን ህዝብ ከትግሬ ጎን እንዲቆም፣ አማራ እና ትግሬን፣ አማራ እና ኦሮሞን አንድ አድርጎ አማራ እያለ መጥራቱን ያቁም” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንትን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ጸሀፊያቸው ልታገናኝን አልቻለችም።
******************************************************************************************************************************************************************************
አፍሪካ ሚስጢራዊ በሆነ ስምምነት ሀብቷን እየተዘረፈች ነው ተባለ
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የቀድሞውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን ፣ የቀድሞውን የናይጀሪያ መሪ ኦለሱጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የኔልሰን ማንዴላን ባለቤት ግራሻ ሚሸልን ያቀፍ የጥናት ቡድን ይፋ ባደረገው ጥናት አፍሪካ ግልጽነት በጎደለው ሚስጢራዊ ድርድሮች የተፈጥሮ ሀብቷን እየተዘረፈች ነው።
ከታክስ ማጭበርበር ፣ በድብቅ በሚካሄድ የማእድን ማውጣት እና በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ውጭ ከመላክ ጋር በተያያዘ አፍሪካ በየአመቱ 38 ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ተመልክቷል።
አፍሪካ በእያመቱ በእርዳታ የምታገኘውን ሁለት እጥፍ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ እንደምታጣ ኮፊ አናን ገልጸዋል። በአጉሪቱ ግልጽነት እንዲሰፍን የአፍሪካ መሪዎች በተጠያቂነት ዙሪያ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ኮፊ አናን ጠይቀዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ባወጣው ጥናት በኢትዮጵያ ባለፉት 9 አመታት ከ11 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ መውጣቱን መዘገቡ ይታወሳል።
Received on Sat May 11 2013 - 13:41:15 EDT