[dehai-news] Ethsat.com: 4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ
4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ
18/09/2013
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው ናቸው።
በ1998 ኣም በሶማሊያ ከእስላማዊ ህብረት ሀይሎች ጋር በተደረገው ውጊያ ተሰታፊ እንዲሁም በዳርፉር የሰራዊት ማስከበር ተልእኮ የዘመቱት እነዚህ የበረራ ባለሙያዎች ሁለቱ ለከፍተኛ ትምህርት ከተላኩት ቻይና ተመልሰው ትግሉን መቀላቀላቸውን ሲገልጹ ሁለቱ ደግሞ ከሳምንት በፊት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ሀይል ምድብ ተነስተው ስርአቱን መክዳታቸው ተመልክቷል።
በቅርቡ የመረጃ መኮንን የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ግንቦት7ትን መቀላቀሉን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወጣቶች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አንዳንድ እግረኛ የሰራዊት አባላትም ድርጅቱን እየተቀላቀሉና ለመቀላቀልም ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
Received on Thu Sep 19 2013 - 12:34:29 EDT
Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved