ይህንን ምን እንበለው? ኢህአዴግ እስካሁን ያለው ነገር የለም
አማርኛ ተናጋሪው በገጀራ ዘግናኝ ግድያ ተፈጸመባቸው
April 15, 2014 07:33 am
“መኖሬን ጠላሁት። ራሴን እንዳልገድል ወንጀል ነው። ሰው እንዳልገድል ወንጀል ነው” በሚል ግራ መጋባት አንድ አዛውንት ይናገራሉ። ተበዳዮች ከእርሻ ስራ በኋላ የሚይዙትን በትር ፖሊስ ሰበሰበ። ከዚያም እገበያ ቦታ ላይ ገጀራና ጦር የያዙ ጎረምሶች እየጮሁ ጥቃት መፈጸም ጀመሩ። 16 ሰዎች፣ 26 ናቸው የሚሉ አሉ ጉዳት ደረሰባቸው። አንድ ሰው ተገደሉ።
ይህ ዜና የተወሰደው ተበዳዮች ራሳቸው ባንደበታቸው ሲናገሩ ከሚታዩበት ቪዲዮ ነው። የተገደሉት አቶ ጌጡ ክብረት ይባላሉ። የሰባት ልጆች አባት ናቸው። የተገደሉት በገጀራ ነው። ከተገደሉ በሁዋላ አይናቸውን አውጥተዋቸዋል። አንደኛው ተናጋሪ አዛውንት እንደተናገሩት ደግሞ “ብልታቸውን ሸንሽነዋቸዋል”።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለህክምና ሲሄዱ “ሂድና አገርህ ታከም። ይህ የእኛ ሃኪም ቤት ነው” እንደተባሉ ምስክሮቹ ይናገራሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በምዕራብ ሸዋ ዞን ደኖ ወረዳ በሶስት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በሚኖሩ የአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ነው።
ሰዎቹ እንደገለጹት ከጎንደር ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ነው ወደ ስፍራው የገቡት። በህጋዊ ማመልከቻና በህጋዊ የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ቀደም ሲል የዝንጀሮ መንጋ የሚኖርበትን ስፍራ እንዳለሙ ይናገራሉ። በዚህም ላይ ህጋዊ ግብር የሚከፍሉ ናቸው። አንድ እድሜያቸው የገፋ ተናጋሪ በቪዲዮው ላይ እንደተናገሩት “አስተዳደሩ ቻፓ (ማኅተም) መትቶ” አስረክቧቸዋል።
ከሃያ ዓመታት በኋላ አሁን “አማርኛ ተናጋሪ ናችሁ። መሬቱን ለቃችሁ ውጡ” የተባሉት ሰዎች ለፌደራል ባለስልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸው ይበልጥ ጉዳት አስከትሎባቸዋል። “እስኪ ምን ታመጣለህ” በሚል ያካባቢው አስተዳደር አካላት ቀልደውባቸዋል። ከሁሉም በላይ ግን ላለፉት ሃያ ዓመታት አብረዋቸው የኖሩ ሰዎች ዛሬ እንዴት ጨክነው ገጀራ አነሱ? የሚለው ጉዳይ ስጋት የሚጭር ሆኗል። በተለይም የፍትህ አካላትና ራሱ ኢህአዴግ፣ ብአዴን ሰው በገጀራ ሲገደል ዝም ማለታቸው ድርጊቱን አሳዛኝ ያደርገዋል።
በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ብሔረሰብ ተወላጆች አሉ። ተስማምተውና ተከባብረው ኖረዋል። አሁንም እየኖሩ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ተዋልደው፣ ወልደውና ከብደው የኖሩ አማሮች ቁጥር ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ አገር መግዛት ከጀመረ በኋላ ኦሮሚያ ላይ በኢንቨስትመንት ስም ሰፋፊ መሬትና የማዕድን ቦታ የያዙ አሉ። ህዝብ እነዚህ ኦሮሚያን እያለቡ ያሉትን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። በተለይም ንጹህ ህሊና ያላቸው ጉዳዩን ከነስሌቱ ይረዱታል። ከነዚህ “ባለጊዜዎች” ዝም ተብለው ምስኪን ጭሮ አዳሪዎች ላይ እንዲህ ያለው ተግባር መፈጸሙ ውሎ አድሮ ወዴት የሚያሰኝ ይሆናል። ነገም በስፋት በተለያዩ ስፍራዎች ድርጊቱ ስላለመቀጠሉ ዋስትና የለም። በሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ላይ።
እነዚህ ከጎንደር እንደመጡና ላለፉት 20 ዓመታት በስፍራው ላይ በህጋዊነት የሰፈሩት ወገኖች እነሱ ካሉት ውጪ ቦታው ላይ መኖር የማይችሉበት ህጋዊ አግባብ ካለ፣ ህጋዊ ጥፋት ወይም የመረጃ ችግር ካለባቸው በህግ ክስ አቅርቦና አስወስኖ አስፈላጊውን ውሳኔ ማሳለፍ ይቻላል። ህግና ስርዓት ባለበት አገር በትር በመንጠቅ ምስኪኖችን በገጀራ ማስደብደብና ማስገደል ዘግናኝ ነው። ሰዎቹ እንዳሉት ሶስት ገበሬ ማህበር የሚሆኑ ናቸው። አንድ ገበሬ ማህበር ውስጥ ባማካይ 600 አባወራ አለ። በሶስት ሲባዛ የአባወራዎቹ ቁጥር ከፍተኛ ይሆናል። አሁንም እነሱ እንደገለጹት እያንዳንዳቸው ባማካይ ስድስትና ሰባት ቤተሰብ አላቸው። እናም ጉዳዩ በቀላል የሚታይ አይሆንም።
“አማራ በሚለው ደማችንና አጥንታችን አትውቀሱን” አልናቸው በማለት ሰዎቹ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የሚደርስባቸው በዘር ነው። ይህ ደግሞ ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት የተከለው አጀንዳ ነው። ህወሃት በፕሮግራም ደረጃ አማራን የማጥፋት እቅድ ይዞ ሲታገል የኖረ፣ አሁን ደግሞ ብአዴን የሚባል ላንቲካ/ሲምቦል ድርጅት አስቀምጦ ይህንኑ የበታችነት ስጋቱ የፈጠረበትን ስሜት እያስተገበረ ነው። ብአዴን ውስጥ ያሉ ወገኖች ግን እስከመቼ በዚህ ይቀጥላሉ?
ለዜናው ጥንቅር የተጠቀምንበትን ቪዲዮ በፍኖተ ነጻነት የተዘጋጀ ሲሆን አዲስ ድምጽ ሬዲዮ ድረገጽ ላይ ነው ያገኘነው – ለመመልከት <
http://www.addisdimts.com/%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8A%93%E1%89%83%E1%8B%AF%E1%89%BD-%E1%8B%B5%E1%88%9D%E1%8C%B5-must-watich-vedio/> እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
ተንቀሻቃሽ ስዕል እዚህ ታች ተመልከት።
የተፈናቃዮቹ ድምፅ
http://www.youtube.com/watch?v=3O5C73bvVGE#t=97
<
http://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2014/04/displaced-muslikm.jpg> ??????? ????? ??? ???????? ?????
ከተፈናቃዮቹ በመከራም ሆነው ሃይማኖታቸውን ይጠብቃሉ
displaced
Received on Wed Apr 16 2014 - 10:31:21 EDT