ልማት ያለ ነፃነትና ፍትሕ ፋይዳ የለውም – (የኔ ትዝብት ከኢትዮጵያ ቆይታዬ መልስ)
ሙሱና! አፈና እና አድልዎ ከማንም ግዜ በላይ በሰፈነበት ሀገር ዘላቂ ፍትሕ! ዴሞክራሲ! ዕድገትና የህግ የበላይነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይወለዳል ብሎ መጠበቅ ነው:: ዛሬ በኢትዮጵያ ሙሱና እና ዓይን ያወጣ ያገር ሀብት ዘረፋ የስርዓቱን ሁለንትናዊ መገለጫ ባህሪይ ከመሆኑም በላይ የህዝባችንን ንሮና ህይወት እየገደለና እያቀጨጨ ያለው ከኤይድስ በላይ ስር የሰደደ ተላላፊ በሽታ እየሆነ መጥቷል:: ዘረፋውም ሆነ አፈናው ከግለ ሰብ አልፎ ወደ ተቋማዊና የተደራጀ ሌብነት በመሸጋገሩ ኢትዮጵያ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና የሌላት” ፍትሕ አልባ የሆነች ሀገር አድርጓታል::
ከ ይኩኖ መስፍን
ቦስቶን ሰሜን አሜሪካ
Friday, October 3rd, 2014 |
እኔ የምኖረው በውጭ ዓለም በሰሜን አሜሪካ ቢሆንም በቅርቡ ለግል ጉዳይና ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ሂጄ ስለነበር ለሶስት ወር ያህል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሬ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በወሬ የምሰማውን ነገር ሁሉ በአካል ተገኝቼ በቀጥታ በሕብረተሰቡ ዘንድ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ምን እንደሚመስል በማየቴ ብዙ ነገሮችን ለመገንዘብና ለመማር ጥሩ ዕድል አጋጥሞኛል::
እኔም “ማየት ማመን ነውና” በቅርብ ተገኝቼ ባንድ በኩል ከህዝቡ አንደበት የሰማሁትንና ያየሁትን እሮሮ በሌላው ገጽ ደግሞ በመንግስት በኩል ያለው ተግባራዊ ምላሽና እንቅስቃሴ ምን እንደሆነ ሰፊው ሕብረተሰብ በተለይም ከሁኔታው ርቆ በውጭ ዓለም በዲያስፓራ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወገን ሁሉ ማወቅ አለበት ብዬ ያሰብኩዋቸውን አንገብጋቢ ጉዳዮች በማንሳት አቅሜ የፈቀደውንና አእምሮየን የዘገበውን ያህል በማካተት የተሰማኝን ስሜትና ተሞክሮ ለማካፈል ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጠቅለል ያለ ሃሳብ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ።………………..
ኣብ`ዚ ታሕቲ ዘሎ ስቱር ሕጥበ-ጽሑፍ [PDF] ጠዊቕካ/ኪ ኣንብቦ/ዮ።
ብርሃነ ሃብተማርያም
Received on Fri Oct 03 2014 - 07:32:59 EDT