Ethsat.com: በዳንሻና ጸገዴ ወረዳዎች አካባቢ የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ
በዳንሻና ጸገዴ ወረዳዎች አካባቢ የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ
18.07.2014
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን
ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው
ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ በትግራይ ክልል በኩል ምን ያክል ታጣቂዎች እንደተሰለፉ ለማወቅ አልተቻለም።
የመከላከያ ሰራዊት ሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው አይታዩም። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑንም ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በብአዴንና በህወሃት ታጣቂዎች መካከል የተጀመረው ግጭት እየሰፋ ሂዶ ኢህአዴግን ሊበትነው ይችላል በማለት እየተናገሩ ነው። የዚህን ዜና ዝርዝር እየተከታተልን እናቀርባለን።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በአዲስ አበባ በረመዳን ጾም ስገደት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በተወሰደ የጭካኔ እርምጃ ብዙዎች ተጎዱ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-”ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች ስልክ በመደወል የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ሲዘጋጁ እንደነበር የኢሳት ምንጮች አስቀድው መረጃ የላኩ ሲሆን፣ በሙስሊም ስም መታወቂያ የተሰራላቸው የደህንነት አባላት ከሙስሊሙ መሃል በመሆን እየጠቆሙ ሲያሲዙ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
Received on Fri Jul 18 2014 - 17:57:41 EDT
Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved