DW.de: አስቸጋሪው የደቡብ ሱዳን ውዝግብና ሽምግልናው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun Nov 23 17:41:09 2014

አስቸጋሪው የደቡብ ሱዳን ውዝግብና ሽምግልናው

ቀን 23.11.2014

ቪዶውን ታች ተመልከት፡

http://www.dw.de/%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B8%E1%8C%8B%E1%88%AA%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%88%B1%E1%8B%B3%E1%8A%95-%E1%8B%8D%E1%8B%9D%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8A%93-%E1%88%BD%E1%88%9D%E1%8C%8D%E1%88%8D%E1%8A%93%E1%8B%8D/a-18079845?maca=amh-standard_feed-amh-11646-xml

ነጭ ዐባይ አቋርጦ የሚያልፍባት የተፈጥሮ ውበትና የደለበ የተለያየ የማዕድናት ሀብት ያላት ፤ ደቡብ ሱዳን ፣ ነጻነት አውጃ 2 ዓመት ከመንፈቅ ከተጓዘች በኋላ ፣ ፕሬዚዳንቷ ሳልቫ ኪር ፣ አምና ታኅሳስ 6 ቀን 2006 ዓ ም፤ መፈንቅለ መንግሥት ሊካሄድብኝ ነበር ሲሉ በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻርና ደጋፊዎቻቸው ላይ ከተነሱ ወዲህ ፣ ደቡብ ሱዳናውያን ፣ ባልታሰበ ሁኔታ፣ በእርስ በርስ ጦርነት እንደገና ፍዳ ሲያዩ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላ ነው።

ይህን ደም አፋሳሽ ውዝግብ ለመግታትና ሰላም መልሶ እንዲሠፍን ለማድረግ የአፍሪቃ ሕብረት በተለይም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት አባል ሃገራት በመሸምገል አያሌ ወራት ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አልቻለም። ለምን? ውጊያው ካልተገታ ፣ ሰላምም ካልሠፈነ የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? በአጎራባች ሃገራት የሚያስከትለው ተጽእኖስ እንዴት ይታያል? አብነቱ ምንድን ነው? «አስቸጋሪው የደቡብ ሱዳን ውዝግብና ሽምግልናው»፣ በሚል ርእስ ፣ዶቸ ቨለ ለዚህ ሳምንት ባዘጋጀው ውይይት 3 እንግዶች ተሳትፈዋል ፣ እነርሱም ፣ በደቡብ ሱዳን የኢጋድ የተቆጣጣሪና አጣሪ ቡድን ዋና ኀላፊ አቶ ተፈራ ሻውል፣ የአፍሪቃ የፀጥታ ጥናት ተቋም ተመራማሪ ፤ አቶ ሃሌ ሉያ ሉሌ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባው የዶቸ ቨለ ዘጋቢ ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ናቸው።

 <http://www.dw.de/%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B8%E1%8C%8B%E1%88%AA%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%88%B1%E1%8B%B3%E1%8A%95-%E1%8B%8D%E1%8B%9D%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8A%93-%E1%88%BD%E1%88%9D%E1%8C%8D%E1%88%8D%E1%8A%93%E1%8B%8D/a-18079845?maca=amh-standard_feed-amh-11646-xml> http://www.dw.de/image/0,,18059328_303,00.jpg ውጊያው ካልተገታ ፣ ሰላምም ካልሠፈነ የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል?




image001.jpg
(image/jpeg attachment: image001.jpg)

Received on Sun Nov 23 2014 - 17:41:09 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved