Goolgule.com: ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 13 Sep 2014 18:27:55 +0200


ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!


ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል

 

September 13, 2014 07:55 am

በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየከረረ የሚሄደው የጥላቻ ደረጃ ያሳሰባቸው “የህወሃት ወዳጆች” ህወሃት ለእርቅ እንዲነሳሳ የማግባባት ስራ እየሰሩ መሆናቸው ተሰማ። የአቶ መለስና “የህወሃት ወዳጅ” ወይም ቅርብ ናቸው የሚባሉት ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል።

 <http://www.goolgule.com/ras-mengesha-leading-the-reconciliation-effort/> የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች እንደዘገቡት ከሆነ በህወሃት መንደር እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ወገኖች በህወሃትና በተቀረው ህዝብ መካከል እየሰፋ የሄደው ጥላቻ መልኩን እንዳይቀይር ከፍተኛ ስጋት አላቸው። በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰማው ቅሬታና የተቋጠረው ቂም ማየሉ ያሳሰባቸው እኚህ ወገኖች ህወሃት ደጁን ለእርቅ መክፈት እንዳለበት በማሳሰብ መጎትጎታቸው እንጂ የእርቁ መሰረትና እርቁ የሚያካትታቸውን ወገኖች በዝርዝር አልገለጹም።

“ኢህአዴግ ናቸው” በሚል የሚታሙት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ፓስተር ዳንኤል ገብረሥላሴ እንደሌሉበት ያረጋገጡት የጎልጉል ተባባሪዎች ከእነ ራስ መንገሻ ስዩምን በተጨማሪ የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ጥላሁን በየነ፣ ፓስተር ዳንኤል መኮንን በዋናነት እንደሚገኙበት <http://www.goolgule.com/ras-mengesha-leading-the-reconciliation-effort/> ጠቁመዋል። ወያኔን በስሙ ከነግብሩ በመጥራት በአገር ውስጥ ሆነው ያለአንዳች ዕረፍት ስለአገራቸው ቀንተሌት የሚለፉት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምን ለማካተት እቅድ እንዳለም አመልክተዋል።

ከሌሎች ምሁራኖች እጅግ በተለየ የሚሰማቸውን ስሜት ያለማቋረጥ፣ ሃላፊነታቸውን ያለድካም፣ እውቀታቸውን ያለገደብ፣ ልምዳቸውን ያለንፍገት በነጻነት ከብሎግ እስከ ፌስቡክ ድረስ ዘመናዊውን ቴክኖሎጂ ሁሉ በመጠቀም እያካፈሉ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን በተባለው እርቅ ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ ስለመሆንና አለመሆናቸው የዜናው ተባባሪዎቻችን ማረጋገጥ አልቻሉም። ሆኖም ግን እውነተኛ እርቅ ሂደት ከተጀመረ ሊያቅማሙ የሚችሉበት ጉዳይ እንደማኖር የዜናው ምንጮች አስረድተዋል። ለዘመናት ካዳበሩት ልምድና በሰላማዊ ትግል ካላቸው ጽኑዕ እምነት አኳያ የፕሮፌሰር መስፍን በዚህ ዕቅድ ውስጥ መግባት ጉልህ ጥቅም አለው፤ ለብዙዎችም በሂደቱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል የሚለው አስተሳሰብ ብዙዎች ይጋሩታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው ግለሰቦች በሙሉ አስተያየት ካላቸው <http://www.goolgule.com/ras-mengesha-leading-the-reconciliation-effort/> ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑንን ይገልጻል።

“በህይወቴ አንዲህ ያለ ጥላቻ አጋጥሞኝ አያውቅም። ህዝብ በጥላቻ ተሞልቷል። ይህ ጥላቻ መልኩን ሳይቀይር ሊመክን ይገባዋል” ሲሉ ለጎልጉል ዘጋቢዎች አስተያየት የሰጡ ምሁር “ኢትዮጵያዊያን በየአቅጣጫው ሊተባበሩና ይህንን አደገኛ ጥላቻ በሰላማዊ መንገድ በእርቅ ሊሰብሩት ይገባል” <http://www.goolgule.com/ras-mengesha-leading-the-reconciliation-effort/> ብለዋል።

ቀደም ሲል ስለ እርቅ ሲጠየቁ “ማንና ማን ተጣላ” በሚል መልስ የሚሰጡት <http://www.goolgule.com/sibhat-and-tplf-to-consider-reconciliation/> አቶ ስብሀት ነጋ ለጀርመን ሬዲዮ “ተቃዋሚዎች አንድ ሆነው ይምጡ፤ ጥያቄያቸውን በጽሁፍ ያቅረቡ” በማለት እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም። አቶ ስብሃት ያለ <http://www.goolgule.com/sibhat-and-tplf-to-consider-reconciliation/> ምንም ምክንያት እርቅን ደጋፊ ሆነው ሊቀርቡ እንደሚችሉ አስተያየት ሰጪዎችን ጠቅሰው የጠቆሙት የጎልጉል ተባባሪዎች “የኢትዮጵያ ህልውና አሁን ካለበት አሳሳቢ አደጋ ስለመድረሱ አቶ ስብሃትና ህወሃት ጠንቅቀው ያውቁታል። የህወሃት ደጋፊዎችና ህወሃት በስማቸው በደል እየሰራ ለጥላቻ የዳረጋቸው ሁሉ ጉዳዩ ዕረፍት ነስቷቸዋል። አሸባሪ፣ ሽብርተኛ፣ ሳይባል ሁሉንም ያካተተ የእርቅ ድርድር ሊዘጋጅ ይገባል” ብለዋል። ዝርዝሩ ብዙ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑንም አልሸሸጉም፡፡

ከተቃዋሚው ዘንድ በተደጋጋሚ የትግራይ ልሒቃንም ሆኑ ሌሎች ባለው አጠቃላይ የአገሪቱ ሁኔታ ላይ ተሳትፎ አያሳዩም፣ በተገቢው ሁኔታ የሚያደርጉት ነገር የለም፣ ከወያኔ ጋር ተሞዳሙደው ነው የሚሠሩት፣ … ሲባል የመኖሩን ያህል አሁን በተጀመረው ሂደት ውስጥ በእንቅስቃሴ ላይ ያሉትን በጭፍን መቃወም ለአገር የሚበጀውን በውል ካለማወቅ የሚመነጭ ጭፍን አስተሳሰብ እንደሆነ <http://www.goolgule.com/ras-mengesha-leading-the-reconciliation-effort/> የዜናው ተባባሪዎች አስረድተዋል፡፡ እርቅ ለመፈጸም ሁሉም ወገን በሚያምነው መወከል አለበት፤ ይህ ደግሞ በአገራችን አሠራር የተለመደ አካሄድ ነው፡፡

በማናቸውም የፖለቲካ እምነት ውስጥ የሚገኙ፣ በየትኛውም የብሄርና የጎሳ ከለላ ውስጥ የታቀፉ፣ አገሪቱ ከገባችበት አስከፊ የጥላቻ አደጋ እንድትጸዳ ከሥሩ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ፤ አለበለዚያም የሙከራቸው መጨረሻው ሳይታወቅ ተቃውሞ ሊሰነዘርባቸው እንደማይገባ የዜናው ምንጮች አስታውቀዋል። ከጅምሩ የማጨናገፍና በጭፍን የመቃወም አሠራር መለመዱ ብዙ የእርቅ ሃሳብና የማስታረቅ አቅም ያላቸውን እያሸማቀቀ ስለሄደ ቢያንስ ጉዳዩን በትዕግስት መመልከት ተገቢ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑት ለጎልጉል ተባባሪዎች አመልክተዋል። አሜሪካ ተቃዋሚዎች ወደ አንድ ህብረት እንዲመጡ ፍላጎት እንዳላት፣ በተለያዩ አገራት በኩልም እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

 

Received on Sat Sep 13 2014 - 12:27:54 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved