Ethsat.com: የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 10 Apr 2015 23:32:22 +0200

የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ

April 10, 2015

ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጧጡፎ በመሸጥ ላይ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

በአለፋ ፣ ጣቁሳ፣ መተማ፣ አርማጭሆ፣ ቋራና በሌሎችም በርካታ ወረዳዎች አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ45 ሺ እስከ 60 ሺ ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጦር መሳሪያዎችን በብዛት የሚገዙት አርሶ አደሮች ናቸው።

በርካታ ቁጥር ያለው የኢህአዴግ ወታደር በጠረፍ ከተሞች ውስጥ ከሰፈረ በሁዋላ የጦር መሳሪያ ሽያጩ መድራቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በቅርቡ በአርማጭሆ የታየው አለመረጋጋት ነዋሪዎች የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን እንዲገዙ ሳያስገድዳቸው እንደማይቀር አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።

የኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተከታታይ የጦርነት ልምምድ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

መንግስት ሰሞኑን የክልሉ ነዋሪዎች የጦር መሳሪያዎቻቸውን አስመዝገበው ህጋዊ ፈቃድ እንዲይዙ መመሪያ አውጥቶ አንዳንድ ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን ሲያስመዘግቡ ታይቷል።

በሻውራ ከተማ ከሰፈሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል አንድ ጌጡ የተባለ ፖሊስ የኦነግ አባል ነህ ተብሎ በመጠርጠሩ ታስሮ ወደ አዲስ አበባ ተወስዷል።

Received on Fri Apr 10 2015 - 17:32:22 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved