ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ተቀያቂዎቹ ተቃዋሚዎቹም ናቸው - ቴድ ዳኘ
27.05.2015 23:28
የዘንድሮው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ተካሄደ፡፡ የምርጫውን ሂደት የታዘበው ብቸኛ ዓለምአቀፍ ተቋም የአፍሪካ ኅብረት ነው፡፡
ለወትሮ የኢትዮጵያን ምርጫዎች ይታዘቡ የነበሩትና አሁንም በዓለም ዙሪያ እየተንቀሣቀሱ የሚታዘቡት የአውሮፓ ሕብረትና የአሜሪካው የካርተር ማዕከል ግን አልተገኙም፡፡ ለምን?
የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑትና የ1997ቱ ምርጫ የኅብረቱ የታዛቢዎች መሪ የነበሩት አና ጎምሽ የአውሮፓ ኅብረት ያልታዘበው ምርጫው “ቧልት ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡
“የአውሮፓ ኅብረት የታዛቢዎችን ቡድን በመላክ ለገዥው ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደ የማስመሰያ ማኅተም መስጠት ስላልፈለግን የደረስንበት የፖለቲካ ውሣኔ ነው” ብለዋል፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን ባለው አቋሙ ዴሞክራሲያዊ፤ ፍትሐዊና ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ብቁ ነው?
“አይደለም ብሎ የሚያሣምነኝ እስካልመጣ፤ አዎ ብቁ ነው” ይላሉ በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ አማካሪ እንዲሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የላካቸው፤ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ስፔሻሊስት ሆነው ለሃያ አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ ቴዎድሮስ ዳኘ፡፡
“ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ችግር አለ የሚባል ከሆነ ብዙውን ጊዜውን እርስ በራሣቸው በመጣላትና በውጭ ሃገሮች በመኖር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተጠያቂነቱን ሊወስዱ ይገባቸዋል” ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ፡፡
ለተጨማሪ ከሁለቱም ጋር በተደረጉ ቃለምልልሶች ላይ የተዘጋጀውን ቅንብር የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡