Facebook.com: የእርዳታ እህሉ እየቀሙት ነው።

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 25 Nov 2015 13:57:04 +0100
Amdom Gebreslasie
November 25, 2ß15

ረሃቡ በሰውና በእንስሳ ሂወት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በመሰራጨት ያለው ጥቂት የእርዳታ እህል ለመዳበርያ፣ ለደደቢት፣ ለማህበራት፣ ለወይን ጋዜጣ ፣ ለኣንቡላንስ ወዘተ እየተባለ እየተቆረጠ ነው። ቅምያው ህዝቡ ክፉኛ እየተቃወመው ይገኛል።

የደጉዓ ተምቤን ወረዳ ሃላፊዎች በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች ኣመራሮች ሰብስበው " እንደ መዳበርያና የደደቢት እዳ ከእርዳታ እህል እንዲያስከፍሉ" ቀጭን ትእዛዝ የሰጡ ሲሆኑ የቀበሌዎቹ ሊቃነ መናብርት "ስልጣናቹ ውሰዱ፣ ህዝባችን በሞትና ሂወት መሃል እያለ እርዳታው ከጉሮሮው መቀማት ኣንችልም" የሚል ኣቋም ይዘው የተከራከሩ ቢሆኑም የዞንና የወረዳ ሃላፊዎች ዳግም ተሰብስበው "የማይታጠፍ የመንግስት ዕቅድ ነው" በማለት በተፅእኖ እንዲቀበሉት ኣድርገዋል።

የደጉዓ ተምቤን ወረዳ ኣይንንብርከኽን ቀበሌ ህዝብ "እርዳታው ሰጥታቹ ተመልሳቹ የምትቀሙን ከሆነ ኣንቀበልም" በማለት እርዳታው ጥሎ ወደ የቤቱ ተመልሰዋል።

የኣይንንብርከኽን ቀበሌ ህዝብ "የቀረበው የእርዳታ እህል ኣነስተኛ ከመሆኑም በላይ የተሰጠችው እርዳታ ተቀብለን ለናንተ የምንመልስ ከሆነ የእርዳታው መቀበል ለኛ ምንም ትርጉም የለውም" በማለት ሳይቀበል ቀርተዋል።

በኣሁኑ ሰዓት በመላ ትግራይ ኣጋጥሞ ያለው ረሃብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኣልጋ ቁራኛ ሁነዋል፣ በረሃቡ ምክንያት እየሞቱም ነው።
መንግስት ህዝቡ ራስበራሱ እንዳይረዳዳ እያስፈራራና እያገደ ይገኛል።

መንግስት በረሃብ እየተጠቃ ላለው ህዝብ በቂ እርዳታ ካለማቅረቡም በላይ ህዝቡ ራስበራስ መተጋገዝ መከልከል፣ የመጣው እህል ለዕዳዎች በማለት ከህዝብ እጅ መቀማት፣ ለኣባይ ግድብ፣ መጋዘን ጠበበ በማለት መዝረፍ፣ ወዘተ ኣሳፋሪ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።

 

‪#‎ክፉ_ቀን‬‪#‎ክፉ_መንግስት‬

‪#‎ክፉ_ረሃብ‬

‪#‎Ethiopian_Famine‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO……!

Received on Wed Nov 25 2015 - 07:57:05 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved