Facebook.com: ማ.ረ.ት "ማዓዝ ረዲኣ ትፈልጥ"( "መች ረድታ ታውቃለች")

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 6 Dec 2015 12:28:08 +0100
Amdom Gebreslasie
December 6, 2015

።።።።።።።።።።።

ስለ ማረት የምትባል የተራድኦ ድርጅ ሰምታቹ ታቃላቹ?
ማረት በትግራይ ህዝብ ስም ከመላ ዓለም እርዳታ ለምና የምታመጣ ግን ረድታው የማታውቅ እድሜ ጠገብ ድርጅት ናት።

ስሟ ህወሓት ማህበረ ረድኤት ትግራይ ብሎ የሚጠራት ሲሆን በትግል ወቅት ደህና ሊባል የሚችል ስራ እንደሰራች ራስዋ ህወሓት ትመሰክራለች።

በሌላ በኩል እንደ ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ ያሉ ወገኖች በ77 ዓ/ም ያጋጠመ ድርቅ ለመከላከል ተብሎ በህወሓት እጅ ከደረሰው እርዳታ 95 % ለማሌሊት መመስረቻና ለብረት መግዣ እንዳዋለችው ለBBC መግለፃቸው የሚታወቅ ነው።

የትግራይ ህዝብ ደግሞ መዓዝ ረዲኣትና ትፈልጥ ( መች ረድታን ታቃለች ) ብሎ ማረት የሚለው ምህፃረተ ቃል ይገልፀዋል።

ከማረት ተገንጥላ የወጣች ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ህዝቡ ነቅላ ለድህነት ያበቃቹ ኣራጣ ኣበዳሪ ድርጅትም ህዝቡ ነቀርሳ ሆናበታለች።

የደደቢት የወለድ መጠን 18% ሲሆን ህዝቡ እንደ ሽንኩርት ነቅላ ጥላዋለች።
የማረት የእድመ ልክ ሓላፊ ኣቶ ተኽለወይኒ ኣሰፋ ሰሞኑን ተሸላሚ ነበረ።

እውነት ኣቶ ተክለወይኒ ከህዝቡ ኣስቀድሞ ተሸልሞ ነበር። ድርጅቱ "መቼ ረድታን ታቃለች" የሚል የክብር ስም።
እሱም ህዝቡ በረሃብ እያለቀ ኣይቶ እንዳላየ ሆኖ ብድሩ እየመለሰ ነው።

እኔ እየገረመኝ ያለው ግን ሽልማቶች ከሞዴል ገበሬዎች ወደ ሞዴል የህወሓት ባለስልጣናት ተቀይሮ ነው መሰለኝ ስብሓት ነጋ፣ ኣዜብ መስፍን ብሎ ተኽለወይኒ ኣሰፋ እያለ እየቀጠለ ነው።

ተኽለወይኒ ይገባዋል ከህዝቡ "መቼ ረድቶን ያቃል" ተብሎ የክብር ኒሻን ተሸልመዋል።
እውይ እንኳዕ ዚኣስ ኣነ ዘይኮንኩ በለት ሂበይ።
እንኳን እቺስ እኔ ኣልሆንኩ ኣለች ዝንጀሮ ምስልዋ በመስተዋት ኣይታ።

‪#‎Ethiopian_Famine‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT ID SO...!

Amdom Gebreslasies Foto.
Amdom Gebreslasies Foto.
Gefällt mirKommentieren
Received on Sun Dec 06 2015 - 06:28:09 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved