የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡
ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል)