Facebook.com: የእርዳታ እህል እየተዘረፈ ነው።

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 8 Dec 2015 15:48:01 +0100
Dec. 8, 2015

==========

በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው ኣንድ እስካንያ መከኒ ከነተጎታቹ የእርዳታ እህል በወረዳው ባለስልጣናትና ነገዴዎች በመመሳጠር የተራገፈ ኣስመስለው በሌላ መኪና ገልብጠው ጭነው ሲወስዱ የኲሓ ህዝብ እጀ ከፈንጅ ይዞ ለፖሊስ ኣስረክበዋል።

እነዚ የወረዳ ባለ ስልጣናትና የኲሓ ነጋዴዎች የዘረፉት በኣራት መኪኖች ጭነው ወደ ነጋዴዎቹ መጋዘንና በራሕለ ወደተባለችው የዓፋር ከተማ ሲያጓጉዙት ተይዘው መቐለ ወኽኒቤት እንዲታሰሩ ተደርገዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ እንደርታ ወረዳ ዓራቶ ቀበሌ የእርዳታ እህሉ እየዘረፉ የተገኙት የቀየሌ ኣመራሮች ህዝቡ እጀከፈንጅ ይዞ ፖሊስ ጣብያ ኣድርሰዋል።

በመላ ትግራይ በድርቅ ለተጠቁ ወገኖች የመጣው የእርዳታ እህሉ ዘረፋ በእጅጉ ተጣጥፎ ቀጥለዋል።

በደቡባዊ ዞን እንዳመኾኒ ወረዳ ችንኮማጆ ቀበሌ ኑዋሪ ህዝብ ለሴፍትነት የመጣው እህል እየዘረፉ ያገኛቸው የወረዳና ቀበሌ ኣመራሮች ይዞ ወደ ፖሊስ ጣብያ በመውሰዱ ከፍተኛ ውጥረት ነግሰዋል።

በእንዳመኾኒ ወረዳ ጎለውሳ ቀበሌ የሚገኙ ኣመራሮች የሴፍትነት እህል የመዳባርያ፣ የማህበራት፣ የኣባይ፣ የመፅሄት ወዘተ እያሉ ያለ ደረሰኝ እየቆረጡለት እንደሚገኙ ታውቀዋል።

በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እየመጣ ያለው የእርዳታ እህል እየተዘረፈ መሆኑ ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪ እንደመሰከሩ የሚታወቅ ነው።

ይሄ ዝርፍያ ከፍተኛ የክልል ባለ ስልጣናት ጀምሮ የወረዳና የቀበሌ ኣመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ህዝቡ በተቻለው መጠን ሌቦች ይዞና ኣጋልጦ ወደ ፖሊስ ጣብያ እያደረሰ ቢሆንም ከሁለት ቀን እስራት ተመልሰው የማስወጣት ተግባር የጠቆመባቸው ህዝብ እያሰቃዩት ይገኛሉ።

የዓረና ኣባላት ሙሉ በሙሉ ከድርቅ እርዳታው ውጭ ተደርገዋል።

‪#‎EthiopianFamine‬.

‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ‬

‪#‎ክፉእ_ዘበን‬

‪#‎ክፉኣት_ካድረታት‬

‪#‎ነፃነታችን_በእጃችን_ነው‬

‪#‎it_is_so‬.

Amdom Gebreslasies Foto.
Received on Tue Dec 08 2015 - 09:48:01 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved