Goolgule.com: ኢትዮጵያ-ተቃውሞ በዝምታ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 9 Dec 2015 18:28:43 +0100

“15 ሚሊዮን ሕዝብ እየተራበ እኛ አንመገብም”

Haromaya University, Harar Campus

* እስካሁን አምስት ሰዎች ሞተዋል

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ጋዜጠኝነት “አሸባሪነት” በመሆኑ መረጃ እንደልብ ባይገኝም ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የተማሪዎች ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

እንደሚነገረው ዘገባ ከሆነ ስማቸውና የመኖሪያ ስፍራቸው የአንዳንዶቹም ከነፎቶዋቸው ይፋ የተደረገው መረጃ ላይ እንደሰፈረው የተማሪዎች ንቅናቄ ከተጀመረ እስካሁን የአምስት ወገኖች ህይወት በህወሃት ታጣቂዎች አልፏል፡፡

ዛሬ የተደረገው ተቃውሞ በበርካታ የተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ሲሰማ በእንቅስቃሴው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

በተለይ በአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ምግብ መመገቢያቸው በመሄድ የምግብ ሰሃኖቻቸውን በጠረጴዛቸው ላይ ካደረጉ በኋላ ግፍ እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት ወገኖቻቸው የኅሊና ጸሎት ካደረጉ በማድረግ 15 ሚሊዮን ሕዝብ እየተራበ፣ ሌላው ደግሞ ከመኖሪያው እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ፣ እየተሰደደ፣ ግፍ እየተፈጸመበት እኛ አንመገብም በማለት የወሰዱትን ምግብ ጠረጴዛው ላይ በመተው ከመመገቢያ አዳራሹ ወጥተው ሄደዋል::

ተማሪዎች እያሰሙ ያለው ተቃውሞ በሌሎች ኃይላት ሳይቀለበስ ወደ አገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀየሩ ህወሃት ለዘመናት የፈራውን ለውጥ እውን ያደርገዋል ተብሎ ቢታመንም እንቅስቃሴውን ከዘር ጋር በማያያዝ ጉዳዩ የአንድ አካባቢ ሰዎች ችግር እንደሆነ አድርጎ ለመውሰድ የሚደረገው ሙከራ ከጥቅሙ ጉዳቱ የበለጠ እንደሚያመዝን ይነገራል፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)

students 1students 2students 3


Received on Wed Dec 09 2015 - 12:28:43 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved