* “(ችግራችን) ትግሪኛ መናገር፤ ትግሪኛ መጻፍ፤ በትግሪኛ መዝፈን፤ አለብህ የሚል ነው፤ እኛ መሽከርከር አንችልም” የወልቃይት ሕዝብ
“እኛ አሁን የምናቀርበው ምንድነው ማንነት ነው፤ አማራነት በማመልከቻ ለማምጣት አይደለም የተነሳነው፤ አማራ ነን፤ ትላንት አማራ ነን፤ ነገ አማራ ነን፤ ለዘላለም አማራ ነን፤ ይኼ አያሳፍረንም፤ እኛ ስንዘፍን፣ ስናለቅስ፣ ስንፎክር፣ ስንሸልል፣ ለቅሶ ስንደርስ፤ ስናመሰግን ለማንኛውም የምንገልጸው በአማርኛ ነው፡፡ ይህ አማርኛችን ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የገኘነው ነው፤ አያሳፍረንም፡፡
“የወልቃይት ሕዝብ አንዲት ጎጆ ተከዜ ተሻግሮ አልቀለሰም፤ ስለዚህ ይህ ምን ማለት ነው፤ የምን ስሜት ነው፤ ሠርጋችንን፤ ሃዘናችንን፤ ደስታችንን የምናወሳውም እንዲሁ ነው፡፡ ለቅሷችንን የሚያውቅ፤ ደስታችንን የሚያውቅ፤ እንጂ በእኛ ላይ አናታችን ላይ መጥቶ አይደለህም፤ አባትህ ሌላ ነው ሊለን አይችልም፤ ማንነት እንደዚሁ ነው የሚገለጸው፤ ማንነት ለቅሶ የምገልጽበት ቋንቋ ነው፤ ማንነት ሳዝን የምገልጽበት ቋንቋ ነው፤ በተለያዩ መልኮ የሚገለጽ ነው፤ እኛ በተለያዩ ሁኔታዎች ከአማራ የሚለየን ምንነት የለም፡፡ ዛሬ ታሪክን የመቶ ዓመት ያደረጉ ሰዎች ሌላ ቋንቋ ሊያወሩ ይችላሉ፤ ታሪክን በትክክለኛ ሁኔታ የገለጹ ምሁራን ግን አማራነታችንን በትክክል ይገልጻሉ፡፡
“24 ዓመት ሙሉ ሕዝባችን እያለቀሰ፤ እንዳይናገር አጎንብሶ እየሄደ ቀና ብሎ እንዳይናገር ያሳፈረው አንድ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ይህም ትግሪኛ መናገር፤ ትግሪኛ መጻፍ፤ በትግሪኛ መዝፈን አለብህ የሚል ነው፤ እኛ መሽከርከር አንችልም፤ … አማርኛችን ጥርት ያለ አማርኛ ነው፤ እንደማንኛውም ተናግረን፤ ጽፈን የምንገልጸው ነው፤ … ስለዚህ ዛሬ አማራ መሆናችንን በማመልከቻ ዕርዱን እያልን አይደለም፤ በደማችንና በሥጋችን፣ በማንነታችን፣ በዘራችን የመጣ አማርኛ ነው፤ (ትግሬ አይደለንም) … ይህ የወልቃይት ሕዝብ ድምጽ ነው፡፡”
ሙሉውን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=Oylot7ehX3w&feature=youtu.be