Ethsat.com: ሶማሊያ ውስጥ የተገደሉ ወታደሮች ሳይታወሱ መቅረታቸው ደማቸው በከንቱ እንደፈሰሰ እንቆጥረዋለን ሲሉ የመከላከያ አባላት ተናገሩ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 15 Feb 2017 23:36:26 +0100

ሶማሊያ ውስጥ የተገደሉ ወታደሮች ሳይታወሱ መቅረታቸው ደማቸው በከንቱ እንደፈሰሰ እንቆጥረዋለን ሲሉ የመከላከያ አባላት ተናገሩ

Feb. 15, 2017
Watch these:

ESAT Daily News Amsterdam February 14,2017

https://ethsat.com/2017/02/esat-daily-news-amsterdam-february-152017/

ESAT DC Daily News Wed 15 Feb 2017

https://ethsat.com/2017/02/esat-dc-daily-news-wed-15-feb-2017/

የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊ ከአስፈልጌ ወየን እስከ ሃልጌን ባሉ ቦታዎች፣ ከሰኔ 1 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተደረገው ጦርነት የ13ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሪጅመንት በርካታ አባላት እንዲሁም በኮሎኔል ጌጡ ዳምጤ የሚመራው ጦር ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል። ይሁን እንጅ ጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቀን ላይ ክፍለ ጦሩና አዛዡ ለሽልማት ቢታጭም ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉ እና ህይወታቸውን የገበሩና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ተራ ወታደሮች በበአሉ ላይ ሳይታወሱ ቀርተዋል። ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ የሞቱ ወታደሮችን ጠርተን ስማችንን አናጎድፍም በማለታቸው ሟቾቹና ቁስለኞቹ ሳይታሰቡ መቅረታቸው የክፍለ ጦሩን አባላት አሳዝኗል። የወገኖቻቸው ደም በከንቱ ፈሷል ሲሉ ሃዘናቸውንም ገልጸዋል።
በህወሃት የሚመራው የመከላከያ ሰራዊት ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይል እውቅና ሳያገኝ ከ70 እስከ 120 ከሎ ሜትሮችን አቋርጦ ወደ ሶማሊያ ድንበር በመግባት ውጊያ ባደረገባቸው የሶማሌዋ ሀልጌ ከተማ እና ገጠራማ አካባቢዎች ህይዎታቸውን ያጡ እና ከባድ አካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ከ100 በላይ መሆናቸውን የሰራዊቱ አባላት ይናገራሉ። 13ኛው ክፍለ ጦር ከአልዙብሪ የአልሻባብ ልዩ ተወርዋሪ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ ፣ ደቡብ ምስራቅ 1ኛ ሪጀመንት ፣ የደቡብ ምስራቅ 138ኛ ሬጅመንት ፣ 178ኛ ሪጅመንት እና 134ኛ ሪጅመንት የተሳተፉ ሲሆን፣ አውደ ውጊያውን ባከሄደበት ሀልጌ ከተማ ደግሞ በሻምበል አወቃቀር 1341ኛ ሻምበል ፣ 1342ኛ ሻምበል ፣ 1343ኛ ሻምበል፣ 1344ኛ ሻምበል፣ 1345ኛ ሻምበል ተሳትፈዋል፡፡
ከፓኪስታን ፣ አፍጋኒስታን እና ሶማሌ የተዋቀረው አልዙበሪ የተሰኘው ከፍተኛ የ አልሻባብ ተወርዋሪ ሃይል ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ሰራዊቱ በተኛበት ከሌሊቱ አስር ሰዓት ላይ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት በሶማሊያ የኢትዮጵያ ውጊያ ያልታየ ከባድ ኪሳራ ደርሷል።
በዚህ እለት በኮለኔል ጌጡ ዳምጤ የተመራው አንድ ሻለቃ ጦር ከባድ ጉዳት ሲደርስበት ኮሎኔሉም ተገድሏል።
በመቶ አለቃ መስፍን ታደሰ መሪነት ስር የነበሩ የ 1341ኛ ሻምበል አባላት የነበሩ የሌሊት ተረኛ ጥበቃ አባላት ፣ በሻለቃ መብራህቱ ተክላይ ስር ግማሽ ሌሊት ጠብቀው ያረፉ የ13ኛ ክፍል ጦር አባላት ፣ በሻለቃ ታደሰ ቀረ ስር የነበሩ የ1343ኛ ሻምበል አባላት ፣ በሻለቃ መብራቲ ተክላይ ስር የነበሩ የ1343ኛ ሻምበል አባላት ፣ የ1345ኛ ሻምበል በሻለቃ አወል ኡስማን ስር የነበሩ አባላት፣ በመቶ አለቃ ተወልደ ብርሃን 134ኛ ሪጅመንት አባል ስር የነበሩ ፣ በሻለቃ አማን ጀማል የተመሩ አባላት እንዲሁም በሻለቃ ያሬድ ጌታቸው 1334ኛ ሻምበል በተመሩ የሰራዊት አባላት ላይ ከፍተኛ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አልዙበሪ የተሰኘው ልዩ ከፍተኛ የአልሻባብ ሃይል አራት ጊዜ በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጉዳት ከባድ ጠቃት የፈፀመ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ጦር ሁለት ቀናት ተኩል በፈጀ የመጠባበቅ ውጊያ የማጥቃት እርምጃ የወሰደው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ትናንት በነበረው የመከላከያ ሰራዊት በአል ላይ የ13ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናንት ጀኔራል አብራሃ ወልደማርያም እና የምስራቅ ዕዝ አዛዥ 4 ጊዜ ከአልሻባብ ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ቢያምኑም፣ እነሱ በአንድ ጊዜ የማጥቃት ርምጃ 60 የአልሻባብ ሰራዊት መግደላቸውን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ከስፈልጌ ወየን እስከ ሀልጌን በነበረው ውጊያ በመንግስቱ ቴሌቪዥን ከታዩት 9 የአልሻባብ አባላት ውጭ ተጨማሪ ታጣቂዎች አለመገደላቸውን ምንጮች ይገልጻሉ።
በረመዳን ፆም ወቅት ከፍተኛ ጥቃት ከአልሻባብ የተሰነዘረበት ሰራዊቱ፣ የሬጅመንት አዛዥ የነበሩትን ኮለኔል ጌጡ ዳምጤ እና በእሳቸው ስር የነበሩትን የሰራዊት አባላት በሞትና በጉዳት አጥቷል። የሟቾቹ ስም ለቤተሰብ ባለመነገሩ ቤተሰብ አልቅሶ እርሙን እንዳያወጣ መደረጉ በሰራዊቱ ውስጥ ሌላው ቅሬታ የፈጠረ ነገር ሆኗል።

Received on Wed Feb 15 2017 - 17:36:28 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved