Goolgule.com: ምግባረ ብልሹዎቹ “የመልካም አስተዳደር” ሰባኪዎች

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 15 Feb 2016 22:07:44 +0100

“ሙስናን መዋጋት መልካም አስተዳደር (ሳይሆን) አርበኝነት ነው!”

corrupt

“የኢትዮጵያ ፓርላማ” እየተባለ በሚጠራው የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ አነጋገር “እስከ እንጥሉ ስለገማው ኢህአዴግና የመንግሥት ሌቦች” ጉዳይ (በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አጠራር “መልካም አስተዳደር” ጉዳይ) ከቀናት በፊት ሪፖርት ቀርቦ ነበር፡፡

አዲስ ፎርቹን ከፎቶው ጋር አያይዞ ያተመው ዜና እንደሚያስረዳው እና ፎቶው በገሃድ እንደሚያሳየው በሪፖርቱ መ/ቤታቸው በአስተዳደር ብልሹነት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙት የኢህአዴግ ሹመኞች አባተ ስጦታው (የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ) እና መድኀን ኪሮስ (የፍርድ ቤቶች ምክትል ፕሬዚዳንት) ከአፈጉባኤው አባዱላ ጋር በቃላት ሰይፍ “ሕዝባዊነታቸውን” ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ጋዜጣው ሹመኞቹን በጓደኞቻቸው ፊት “ሲያጉረመርሙ” ተሰሙ ቢልም፤ በርካታ ማኅበራዊ ሚዲያዎች “ዱላ ቀረሽ” ግብግብ ብለውታል፡፡

ጋዜጣው እንዳለው ከሆነ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከዚህ በፊት የሶስት ቀናት የቅሬታ ሰሚ ጉባኤ ጠርቶ በነበረበት ጊዜ ተሳታፊዎች ያለባቸውን ቅሬታ ሲያሰሙ የከተማው ም/ቤት አፈጉባኤ ታቦር ገ/መድኅን “ይህ ስብሰባ የተጠራው ትልቅ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እንጂ የናንተን ተራ አቤቱታ ለመስማት አይደለም” በማለት አቃለውባቸው ነበር፡፡

ደራሲና ገጣሚ ካርል ክሮስ እንዳለው “ሙስና ከሴተኛአዳሪነት የከፋ ነው፡፡ ሴተኛአዳሪነት የአንድን ግለሰብ ሞራል አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን ሙስና ግን የአንድን አገር ሞራል አደጋ ላይ ይጥላል”፡፡ ከዚህ አንጻር ይመስላል የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህንን ያሉት “ሙስናን መዋጋት መልካም አስተዳደር አይደለም፤ ራስን መከላከል ነው፤ የአገር ፍቅር ነው፤ አርበኝነት ነው!” (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)

Received on Mon Feb 15 2016 - 16:07:47 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved