Zehabesha.com: ሰልፈኞች ንብረትነቱ የሕወሓት የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ አቃጠሉ – ወደ አ.አ. የሚያገናኙ መንገዶች በ20 አቅጣጫዎች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰማ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 17 Feb 2016 00:24:29 +0100

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ የስርዓቱን ንብረቶች ወደ ማውደም ተሸጋገረ:: ቀደም ባለ የዘ-ሐበሻ ዜና ም ዕራብ አርሲ ቀበሌ ጽህፈት ቤት መቃጠሉን የዘገብን ሲሆን አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ በምስራቅ ሸዋ ንብረትነቱ የትራንስ ኢትዮጵያ የሆነ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ በሰልፈኞች ተቃጥሏል::

Oromo
ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ስም ከፍቶት ሆንም ግን አንዳችም ቀን የትግራይን ሕዝብ ጠቅሞ የማያውቀው ኤፈርት ስር የሚገኘው ይኸው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት ቦቴ በሰልፈኞች ከተቃጠለ በኋላ ወደዚያው ለመንዳት የሚፈልጉ ሹፌሮች ስጋቱ እንዳየለባቸው ለማወቅ ተችሏል::

ይህ የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው ቦቴ መኪና የተቃጠለው ባቱ ከተማ ውስጥ ነው::

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የሚያስኬዱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች መዘጋታቸው ተሰምቷል:: በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ 20 አካባቢዎችሕዝብ መንገድ ዘጋግቶ ተቃውሞውን እየገለጸ ባለበት በዚህ ሰዓት የአጋዚ ሰራዊት መንገዶችን ለማስከፈት ወደ ህዝቡ እየተኮሰ እንደሚገኝ የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ::

እንደ መረጃዎች ከሆነ በአሁኑ ወቅት በነዚህ መንገድ በተዘጋጋባቸው አዲስ አበባን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በሚያገናኙ መንገዶች ማንናውም መኪና የማይተላለፍ ሲሆን የጸጥታ ስጋቱም እንዳየለ ነው::

*******************************************************************************

ሰልፈኞች በአዶላ የቀበሌ ጽሕፈት ቤት አነደዱ

shashemene 23

(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አርሲ በተለይም ሻሸመኔ ከተማና አካባቢዋ ባሉ ከተሞች ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው:: በተለይ በሻሸመኔና አካባቢዋ ባሉ ከተሞች የሕዝቡ ቁጣ ለ5 ተከታታይ ቀናት እንደቀጠለ ሲሆን መንገዶች ተዘጋግተው ሕዝቡ ከአጋዚ ሠራዊት ጋር መፋጠጡ ተሰምቷል::

ለሻሸመኔ ቅርብ በሆነችው አዶላ መንደር የአጋዚ ጦር መሰብሰቢያ እንደሆነ የሚነገርለት ቀበሌ ጽህፈት ቤትን ሰልፈኞች በ እሳት ያነደዱት ሲሆን የቢሮ እቃዎችንም አውጥተው አደባባይ እንደጣሉት ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ጠቁመዋል::

በዛሬው ዕለት በአርሲ ከተማ አጋዚ ሠራዊት አሁንም እርምጃዎችን እንደወሰደ የጠቁሙት የዜና ምንጮቻችን ጉዳዩ ከቁጥጥር ሥር ከመዋል አልፏል:: በትናንተናው ዕለት እስር ቤት ከፍተው ከ100 በላይ እስረኞችን ማስለቀቃቸውን ዘ-ሐበሻ መዘግቧ ይታወሳል:: ዛሬ ደግሞ የቀበሌ ጽህፈት ቤት በ እሳት ተቃጥሏል::

በአዶላ ከተማ አጋዚ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰልፈኞች መቁሰላቸውም ተሰምቷል::

በሻሸመኔ የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ለማብረድ የፌደራል ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸው ታውቋል::

ባሌን እና መካከለኛው የመሃል ሃገር ከተሞችን የሚያገናኘው መንገድ ሻሸመኔ ላይ ሰልፈኞች እንዴት እንደዘጉት የሚያሳይ ፎቶ ከታች ይመልከቱ::

shashemene

Received on Tue Feb 16 2016 - 18:24:29 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved