Sunday, February 28th, 2016
መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል።
የሚል መንደርደሪያ በመሆኑ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ በሁለት ጎራ ተከፍሎ እንዲጋጭ አይነተኛ መንገድ ተከፍቷል።
በተለይም የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችና የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገናዊ ተቆርቋሪዎች… ከአመራር ጀምሮ እስከ ጓድ መሪ ድረስ የስልጣን እርከን ዉስጥ የሚገኙ… የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ጦርነት መመረጡ አግባብ አይደለም! አርበኞች ግንቦት7ም ሆነ ኦነግ ወገኖቻችን ናቸዉ መንግስት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ልዩነቶችን ለመፍታት ያደረገዉ ጥረት የለም! ለምን ጦርነት እንደ መፍትሄ ይወሰዳል? በሚል እስተሳሰብ እርስ በእርሱ እየተመካከረ ሲሆን ..ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ሰራዊቱ እየተሰወረ ለመሆኑ ታማኝ ምንጮቻችን ገለጸዋ።
በተለይም ከሁመራ ጀምሮ እስከ አማሃጅር ድረስ ለማጥቃት በዝግጅት ላይ የሚገኘዉ በሜካናይዝድ ክ/ጦር የተዋቀረዉ የተዉጣጣ ሰራዊት በየቀኑ ክፍተት እያመጣ መሆኑ ወያኔን ከባድ ችግር ዉስጥ ከቶታል፣ አንዳንድ አመራሮችን ባለማመን ምክንያት ከፍተኛ ጄኔራሎች መሬት ወርደዉ እየሰሩም እንደሆነ ታውቋል፣ የአየር ሐይል ሄሊኮፍተር አብራሪዎች ቦታ በብዛት በትግሬዎች እንዲያዝ ተደርጓል።
በባድሜ በኩል በተመሳሳይ መልኩ በአየር ሐይል የታገዘ ዉጊያ ለማድረግ ዝግጅቱ እየተጧጧፈ ሲሆን ደብረ ዘይት እና ድሬ ዳዋ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ የአየር ሕይል 70% ለትግራይ ነጻ አዉጭ የስልጣን ማራዘም ፍላጎት ሲባል ብቻ.. ወደ መቀሌ ተወስዶ በባድሜ በኩል የሚወረወረዉን የወያኔ እግረኛና ሜካናይዝድ እንዲያግዝ ንድፉ በወያኔ የጦር መሐንዲሶችና ጄኔራሎች የቀረበ ቢሆንም… በዚህ በኩል ለሚደረገዉ ማጥቃት ሻቢያ ከፍተኛ ዝግጅት እንዳላት እና በዚህ ክንፍ ለምናደርገዉ ማጥቃት በአንድ ብሔር ብቻ ማለትም በትግሬ ህዝብ ብቻ እንደምንዋጋ እንድታዉቁ ምክንያቱም ሌሌች የኢዮጵያዊ ብሔሮች ከእንግዲህ ለእኛ እንጂ ለሐገራቸዉ የሚሞቱ አይመስላቸዉም በማለት የፖለቲካ ወታደራዊ መረጃ ክፍሉ በድፍረት መናገሩን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።