Goolgule.com: “ትውልድ አምጿል!” -“(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው” ሙላቱ ገመቹ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 13 Aug 2016 22:21:51 +0200

“ትውልድ አምጿል!”

“(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው” ሙላቱ ገመቹ
mass protest

“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”፡፡ “(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው”፡፡

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ የጠቀሳቸው ሁለት ግለሰቦች የተናገሩት ነበር ከላይ የሰፈረው፡፡ ጋዜጠኛው ዘገባውን ሲጀምር “ኢትዮጵያ እየተሰነጣጠቀች ነውን” በማለት ይጠይቅና በሁሉም አቅጣጫ ያለውን አመለካከት ያሰፍራል፡፡ (ከዜና ዘገባው ጋር Violent Protests in Ethiopia በሚል ርዕስ የጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ በወጣ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን  አሰቃቂ ግፍ እና ጨካኝ ድብደባ እዚህ ላይ መመልከቱ የግድ ይላል)፡፡

ልማት” አካሂዳለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች አለመመለሱን የሚያትተው ዘገባ የዓለምአቀፍ ቀውስ ቡድን ተመራማሪ የሆኑትን ራሺድ አብዲ “ይህችን አገር አንድ አድርጎ ወደፊት ለመግፋት ሁልጊዜ አስቸጋሪ” እንደሆነ በመጥቀስ አሁን ለሚታየው ሕዝባዊ ዓመጽ ማብብራሪያ ይሰጣል፡፡

protest 3ኢኮኖሚውን አሳድጌአለሁ የሚለው ኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት መግፈፉንም አብሮ እንዳሳደገው የሚናገረው የዜና ትንተና በአገር ውስጥ የሚደረገው አፈና፣ ግድያ፣ እስር፣ እንግልት፣ … በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ምስክርነታቸውን ሲሰጡበት የቆየ መሆኑን ያስረዳል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚቀርበው አቤቱታ ስፍር ቁጥር የለውም፤ መሬት ከመንጠቅ ጀምሮ የፓርላማ ወንበርን መቶ በመቶ የራስ እስከማድረግ እና የአንድን ቡድን የበላይነት ከፍ እስከማድረስ የዘለቀ ነው፡፡ ይህም በየጊዜው የፈጠረው ምሬት አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ እንዲደረስ አድርጎታል፡፡

በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ስዩም ተሾመ የተናገሩትን የዜና ዘገባው ይጠቅሳል፤ “ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”፡፡

ለዚህ አገር አቀፋዊ ዓመጽ ምክንያቶች ናቸው ያላቸውን ሦስት ነጥቦችን ጋዜጠኛው ያነሳል፤

  1. ልባምስልኮች – ዘመናዊዎቹ “ስማርት” ስልኮች (ልባምስልኮች) በርካታ መረጃ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት አገዛዙ እንደፈለገ እየከፈተ የሚዘጋው ቢሆንም እንኳን ወጣቱ ትውልድ እነዚህን ስልኮች በመጠቀም ፎቶ በማንሳት፤ ቪዲዮ በመቅረጽ፤ በማኅበራዊ ድረገጾች በማስተላለፍ መረጃ ይለዋወጣል፡፡ ወጣቶች በነዚህ ስልኮች ግንኙነት በማድረግ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸውን ጋዜጠኛው እማኝ አድርጎ ይጠቅሳቸዋል፡፡protest 1
  2. በአማራና በኦሮሞ ወገኖች በመካከል የተፈጠረው የጋራ እንቅስቃሴ ሌላው ተጠቃሽ ነጥብ ነው፡፡ ህወሃት የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም በሁለቱ መካከል ልዩነትን እያሰፋ የተጠቀመበትና በታሪክ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ቁርሾ በህወሃት አማካኝነት ለተፈጠረው በደል እንዲተባበሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ሁኔታዎች መቀየራቸውን በመናገር ጋዜጠኛው በኦሮሞ ትግል ውስጥ አመራር የሆኑት ሙላቱ ገመቹ “(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ የትብብሩን አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በአናሳነት የሚጠቀሰው የትግራይ ክፍል (ስድስት በመቶ ነው) የአገሪቱን የወታደራዊ፣ የስለላ፣ የደኅንነት፣ የንግድና የፖለቲካ መዘውሩን በእጁ ማስገባቱን በመጥቀስ የግፍ መበራከት ሁለቱን ወገኖች አስተባብሯቸዋል የሚል እንደምታ ይሰጣል፡፡
  3. ህወሃት እንደ መለስ ዓይነት መሰሪ መጣቱ አሁን ለሚታየው ተቃውሞ እንቅስቃሴ ምክንያት እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል፡፡ መለስ የሚመጣባቸውን ውድቀትና ጥፋት አስቀድሞ በማየት ወጥመድ ከማዘጋጀት እስከ ማለሳለስ ድረስ የመጠቀም ብቃት የነበራቸው መሆኑን በማብራራት የመለስ ጫማ የሰፋቸው የደቡቡ ኃይለማርያም ደኅንነቱንና ስለላውን በሚቆጣጠሩት ትግሬዎች አመኔታ እንደሌላቸው ይናገራል፡፡

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የበለጠ ደም መፋሰስ እንደሚኖርና አሁንም በየማኅበራዊ ድረገጾች እንዲሁም ተቃውሞ በተደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ከጥላቻ ጀምሮ እስከ ጥቃት የዘለቀ በግልጽ የሚታይ እንቅስቃሴ እንዳለ ጋዜጠኛ ጌትልማን ይናገራል፡፡

የምዕራብ ተላላኪና አሽከር በመሆን በሥልጣን ለመቆየት የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ከአንጋሾቹ በሚያገኘው ዕርዳታ ዜጎችን መግደሉና መብቶችን ማፈኑ ምዕራባውያንን ባልፈለጉበት ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡ የህወሃትን አሠራር ለመቃወምም ለመንቀፍም አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡ ዴሞክራሲን መጨፍለቅና ሎሌያቸውን መደገፍ ወይም ፊታቸውን ማዞርና ከህዝብ ጋር መቆም!protest 2

ራሺድ አብዲ ይህ ሁኔታ ምዕራባውያንን “በጣም ቀጭን በሆነ ገመድ ላይ እንዲራመዱ እያደረጋቸው ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ ዘገባው ያበቃል፡፡

የትውልድ ዓመጽ” የሆነው የሰሞኑ የነጻነት ጥያቄ ህወሃትን ብቸኛ እያደረገው እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ አፍቃሪ ህወሃት የሆኑ በኦሮሞና በአማራ መካከል ልዩነቶች መኖራቸውን በመናገር አሁንም ልዩነቶችን ለማስፋት የሚደርጉት ሙከራ የበለጠ የመለስን እኩይ ባህርይና “እውነተኛ ውርስ” በግልጽ ያስረዳ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን አሁን በኢትዮጵያ የተነሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአንድ ፓርቲ ወይም ቡድን የተቀሰቀሰና ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ ሳይሆን የሕዝብ ዓመጽ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ ህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን በያዘ ጊዜ ህጻናት የነበሩ ወይም ገና ያልተወለዱ፤ ህወሃት ግፍ እየፈጸመ ለዓቅመ ዓመጽ ያደረሳቸው ናቸው፡፡

“ትውልድ አምጿል”!

Received on Sat Aug 13 2016 - 15:00:56 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved