Ethsat.com: በአማራ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደሌሎች አካባቢዎችም እየተስፋፋ ነው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 29 Aug 2016 23:58:53 +0200

በአማራ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደሌሎች አካባቢዎችም እየተስፋፋ ነው

ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008)

August 29, 2016

Watch these news:

Latest News August 29,2016

http://video.ethsat.com/?p=27681

http://video.ethsat.com/?p=27686

ESAT Daily News Amsterdam August 29,2016

http://video.ethsat.com/?p=27706

በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘው ሳምንት ወደ አዳዲስ አካባቢዎች መዛመቱን ተከትሎ፣ የአገዛዙ ሃላፊዎች በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንደገቡና ህዝባዊ ተቃውሞንም በሃይል ለመጨፍለቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ እንደሆነ ተነገረ። ህዝባዊ ተቃውሞ በተለይም በሰሜን በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ አድማሱን በማስፋት በሌሎች በትናንሽ ከተሞች ጭምር በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ ታውቋል።

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ በምዕራብ ጎጃም፣ አዊና፣ ምስራቅ ጎጃም ከተሞች፣ ባሕር ዳር፣ ፒኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ አቸፈር፣ ቋሪት፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ (ኮሶበር)፣ ቲሊሊ፣ ቡሬ፣  ፍኖተ ሰላም፣ ብርሸለቆ፣ ጃቢ ጠህናን፣ ሽንዲ፣ ደምበጫ፣ የጨረቃ፣ አንበር፣ ሎማሜ፣ ፈረስ ቤት፣ አዴት፣ ይልማና ዴንሳ፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ሞጣ፣ ጉንደወይን ተስፋፍቶ የምዕራብና የምስራቅ ጎጃም አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ከመንግስት አገዛዝ ቁጥጥር ውጭ ማድረጉ ታውቋል።

የክልሉ ባለስልጣናትና የህወሃት አመራሮች ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከቁጥጥር ውጭ ከመውጣቱ በፊት በሃይል ለመቀልበስ እየተመካከሩ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በቀጣይ የሚወስዱት እርምጃ ምን መሆን አንዳለበት እየመከሩ እንደሚገኙ የሚናገሩት የኢሳት ምንጮች፣ ተቃውሞው ወደ ወሎና ሰሜን ሸዋ እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንዳለበት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ህዝባዊ ተቃውሞው በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ሳይገደብ በቤት ውስጥ አድማም ተጀምሯል። በጎንደር ወረታ ፣ ጋይንት ፣ ደብረታቦር እስቴ የቤት ውስጥ ኣድማውን መቀጠላቸው ታውቋል። በጎንደር ከተማ የስራ ማቆም አድማው ላለፉት 6 ቀናት እየተካሄደ መሆኑን የተናገሩት የኢሳት ምንጮች፣ በፍኖተ ሰላምም የቤት ውስጥ አድማው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በብር ሸለቆ የአርሷደር ታጣቂዎች ከወታደሩ ጋር ግጭት ተፈጥሮ ቁጥራቸው ያልታወቁ የመንግስት ወታደሮች እና ታጣቂ ገበሬዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ለኢሳት መረጃ ያደረሱ እማኞች ከስፍራው ዘግበዋል።

*******************************************************************************

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተከትሎ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እየወጡ ነው ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008)

August 29, 2016

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱ አስፍቶ መላው ሰሜን ጎንደርን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ምዕራብ ጎጃምን፣ አዊን እና ምስራቅ ጎጃምን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እያወጣ መሆኑ ተገለጸ።

በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የአገዛዙ መዋቅር እየፈራረስ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ምዕራብ ጎጃም ባሉ ከተሞች ማለትም ባሕር ዳር፣ ፒኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ አቸፈር፣ ቋሪት፣ ፍኖተ ሰላም፣ ብርሸለቆ- ጃቢጠናን፣ ቡሬ፣ ሽንዲ፣ ደምበጫ፣ የጨረቃ፣ አንበር፣ ሎማሜ፣ ፈረስ ቤት፣ አዴት ይልማና ዴንሳ፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ሞጣ፣ ጉንደወይን ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍና የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ተካሄዷል።

በየጊዜው የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እና በቤት የመቀመጥ አድማ መደረጉ የአገዛዙን ባለስልጣናት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ለማወቅ ተችሏል።

በዛሬው ዕለት በባህርዳር የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ወደ አደባባይ ተቃውሞ በመቀየሩ ወደ ከተማዋ የሚወጡና የሚገቡ መንገዶች መዘጋታቸው ታውቋል። በከተማዋ የተኩስ ዕሩምታ ይሰማ እንደነበር የገለጹት የኢሳት ምንጮች፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ መድረሱ ተነግሯል።

በከተማው የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አይሎ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣቱ፣ የመንግስት ሃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ ተኩስ በመክፈት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ህዝባዊ ማዕበሉን የፈሩት የመንግስት ሹማምንቶች በህወሃት/ኢህአዴግ ጦር እየተጠበቁና አንዳንዶቹም እየሸሹ እንደሆነ ለማወቅ ለኢሳት ከደረሰው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አዊ ዞን ውስጥ የምትገኘው የቻግኒ ከተማ በከባድ ሕዝባዊ ተቃውሞ እየተናጠች እንደምትገኝ ታውቋል። ወደ አደባባይ የወጣው ሰላማዊ ሰልፈኛ፣ በሕወሓት/ኢህአዴግ ካድሬዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል በሚል ስጋት የካድሬ ቤቶችና የአገዛዙ መስሪያ ቤቶች ጭምር በመከላከያ ሰራዊት ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ኢሳት ያነጋገራቸው እማኞች ከስፍራው ገልጸዋል። ትናንት ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲያደርጉ የነበሩ የእንጅባራ (ኮሶበር)፣ ዳንግላ እንዲሁም በጎንደር ስማዳ ህዝብ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ተቃውሞ ሲያደርጉ እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።

በዛሬው ዕለት በጎንደር ሃሙሲት እና ወረታ መሃል፣ ጉማራ ድልድይ ላይ በመንግስት ሃይሎች እና በአርሶደአሮች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 7 ፌደራል ፖሊሶች እና 4 አርሶአደሮች መሞታቸው ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ከሳምንታት በፊት በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶ መላውን የምዕራብ ጎጃም፣ የአዊ እና የምስራቅ ጎጃም አካባቢዎች ማዳረሱ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራውን መንግስት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል።

******************************************************************************

ከፍተኛ ቁጥር ያለው መደበኛ ሰራዊት ወደ አማራ ክልል እየተንቀሳቀሰ ነው

ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008)

August 29, 2016

ህወሃት በአማራ ክልል እየተካሄደው ባለው ህዝባዊ ንቅናቄ በድንጋጤ ላይ የሚገኘው የህወሃት አገዛዝ፣ በጎንደር፣ ጎጃም፣ አዊ ዞኖች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለማስቆም እንዲያግዙ ከ2ሺ በላይ የአጋዚ ጦር አባላትን  ከአዲስ አበባ ትናንት ዕሁድ ወደ አማራ ክልል ማንቀሳቀሱ ተገለጸ።

በአማራ ክልል በጎጃምና ጎንደር የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የተረዳው የህወሃት አገዛዝ፣ ተቃውሞን በሃይል ለማስቆም መደበኛ ወታደርና የአጋዚ ገዳይ ቡድን በከተሞች አሰማርቶ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በመግደልና በማስፈራራት ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለመቀልበስ እንዳቀደ ከስፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቃውሞ በሚደረግባቸው ከተሞች የሰልፉ አስተባባሪ ናቸው የተባሉትን ወጣቶችን ለመያዝና ተቃውሞውን ለማስቆም ጥረት እንደሚያደርግ ከአማራ ክልል የኢሳት ምንጮት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአጋዚ ወታደሮች ወደ አማራ ክልል ገብተው የክልሉን ወጣቶች በአልሞ ተኳሽ መሳሪያ ከመጨረሳቸው በፊት፣ ህዝቡ ከየአካባቢው በነቂስ  በመውጣት መንገድ በመዝጋት ጉዟቸውን እንዲያስተጓጉል ጥሪ ተደርጓል።

በብዓዴን አባላት ላይ ጥርጣሬ እያየለ የመጣው ህወሃት፣ በአማራ ክልል የኖሩ የህወሃት አባላት የሆኑ ሲቪል የለበሱ ሰላዮችን በማሰማራት ሰልፉን ያስተባብራሉ የተባሉትን ወጣቶችን እየለዩ እንዲሰጡ ማድረጋቸው ተነግሯል። በእንጅባራና ዳንግላ ከተሞች የህወሃት አባላትና ሰላዮች ሰላማዊ ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች ላይ በመተኮስ የሰው ህይወት እንዳጠፉና እንዳቆሰሉ ከስፍራ የደረሰን ዜና የመለክታል።

 
Received on Mon Aug 29 2016 - 16:37:57 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved