አገሪቱ ያለችበትን ውጥረት ተከትሎ ትናንትና የኢህአደግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚያወጣው መግለጫ በጉጉት ይጠበቅ የነበረ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአመራር ብቃት የሚፈተሽበት ነው ተብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን የተሰጠው መግለጫ በአባላቱ ዘንድ ኢህአደግ ለመንኮታኮቱ ማረጋገጫ እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ከመግለጫው ይጠበቅ የነበረው በወልቃይት አማራ ማንነት በተመለከተ የሚወሰን ምን ይሆናል የሚለው ነበረ፡፡ አባላቱ የጠቁት
1. የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ ምለሽ ተሰጥቶበታል
2. የፈዴራል መንግስት ከትግራይ ክልልና ከአማራ ክልል መንግስታትን በመምራት የሚያስተካክለው ይሆናል
3. የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል
4. በወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ ምክንያት የታሠሩት በሙሉ እንዲለቀቁ ተወስኗል
5. የሕዝቡን እንቅስቃሴ ተጠቅመው ሕገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሠማሩ ግለሰቦችን ለመከላከል ሲባልበተወሰደው እርምጃ አንዳንድ ንጹሀን ሰዎች ላይ ስለደረሰው ሟቿች ቤተሰብ መንግስት መጽናናትን የሚመኝ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ የሚክስ ይሆናል፡፡
6. ከዚህ በኋላ መንግስት በወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡን ይሁንታ ያገኘ ውሳኔ ይሰጣል የሚለውን ያካተተ ውሳኔ እንደሚገለጽ ከመጠበቁም በላይ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንዲሰጥ ከፍተኛ ግፊት ሲደረግ ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚው የወልቃይትን ጥየቄ መፍታት ለትግራይ ክልል የሰጠ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመሆኑም በኢህአደግ አባላት የሚከተለው ታምኖበታል፡፡
1. ብአዴን በአማራ ክልል እግሩን የሚያሳርፍበትን ሥፍራ አጥቷል
2. ትግራይ ክልል አማራን በመውረር ማስተዳደር አትችልም
3. የአማራን ሕዝብ ገድሎ መጨረስ አይቻልም
4. የወልቃይት ጉዳይ ለዘላለም የማይፈወስ ካንሰር ነው
5. አማራ ክልል ለነፃነት ኃይል ነን ለሚሉት የጸዳ ነፃ ቀጠና ሆኗል
6. ኦሮሚያ በጥቂት ጊዜ የአማራን መንገድ ይዞ ነጻ ቀጠና ይሆናል
7.የመንግስት ባለሥልጣናት በየፊናው ለመሸሽ ተዘጋጅተዋል የሚል ታምኖበታል፡፡
በመሆኑም የኢህአደግ አባላት ወዴት እንደሚሸሹ ግራ ከመጋባቱም በላይ ፍርክስክሱ መውጣቱ መታየት ጀምሯል፡፡ የየአዲስ አበባ ሕዝብም ዘሎ ለመያዝ እንዳደፈጠ ነብር ተገምቷል፡፡ ይህ እንፎርሜሽን ከወደ ፓርላማ አባላት የተሰበሰበ