(ዘ-ሐበሻ) በመላው ኢትዮጵያ ገዢው የሕወሓት መንግስት ሕዝብን በየፊናው እያሰቃየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝብ የራሱን እርምጃ በባለስልጣናቱና ጠመንጃን በታጠቁ ሰዎች ላይ መወሰድ ጀምሯል:: ዛሬ በአዲስ አበባ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 17 የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና አንድ የወረዳ ከፍተኛ ባለስልጣን መገደላቸው ታውቋል::
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በተለምዶው ሃና ማርያም አካባቢ የሕዝብን ቤት ለማፍረስ የተያዘውን እቅድ ለማስፈጸም የከተማው አስተዳደር ከሕዝቡ ጋር በተፋጠጠበት ወቅት ከሕወሓት ደህንነት ቢሮ የተላኩ ሰምቶ አደሮች ባነሱት ግርግር የተነሳ; ተነሳ በተባለው ግጭት ፖሊሶች ወደ ህዝብ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡ የራሱን እርምጃ በመውሰድ በ17 የፖሊስ አባላት እና በወረዳው ባለስልጣን ላይ እርምጃ ወስዷል::
ከህዝቡም ወገን በርካታ ሰዎች እንደቆሰሉ የተሰማ ሲሆን ፖሊሶችም እንዲሁ እንደተጎዱ መረጃው ይጠቁማል::
ይህንን ብጥብጥ ህዝብ እንደጀመረው ለማስመስል የደህንነት አባላቱ ተንኩሰው መሰወራቸውን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሆን ብሎ ቤቴ አይፈርስብኝም ያለውን ህዝብ ለማሸማቀቅ ነው ብለዋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ መንግስት በዛሬው ብጥብጥ 1 ፖሊስ እና አንድ የወረዳ ባለስልጣን መገደሉን ገልጾ ጥቃቱን ሕገወጦች ያደረሱት ሲል ወንጅሏል: