Amharic.Voanews.com: "የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው" ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 2 Mar 2016 00:34:24 +0100

በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

ትዝታ በላቸውመለስካቸው አምሃ

በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

የማንነት ጥያቄ ደግሞ ከአሰፋፈርና ከመሬት ይዞታ ጋር በጥብቅ የተሣሰረ ነው። ይህ ጉዳይ በክልሎች ቅርፅና ይዘት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ይህ ምናልባት የማንነት ጥያቄ በሚነሣሳባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚያጋጥም ላይሆን ይችላል።

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አቅንተን የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በየጊዜው ስንዘግብ ቆይተናል።

በወልቃይት አማርኛ ተናጋሪው ሕዝብ፤ አስተዳደሩ ከፍላጎታችን ውጭ ወደ ትግራይ ጠቅልሎናል ሲል ተቃውሞ ካቀረበ ሰነባብቷል።

ቅሬታውንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሞ አባላቱ አዲስ አበባ ከመድረሳቸው በፊትና ከደረሱም በኋላ እየተዋከቡ መሆናቸውን አስታውቋል።

አሁንም ከፍተኛ የባህልና የሥነ-ልቦና ተፅዕኖ  እያደረሱብን ነው ሲሉ ያካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በቀዳማዊ ኃይለሥሌ ዘመነ-መንግሥት ለብዙ ዓመታት የጠቅላይ ግዛቱ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምንም ይዘናል።

ትዝታ በላቸው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሁለት የወልቃይት አዛውንት አነጋግራለች። የመጀመሪያው አቶ ላቀው አንዳርጌ ይባላሉ።

የኢትዮጵያ ካርታየኢትዮጵያ ካርታ

ትዝታ ያነጋገረቻቸው ሌላኛው የወልቃይት አካባቢ ተወላጅ ደግሞ የሰማንያ አምስት ዓመቱ አዛውንት አቶ ብርሃኑ አስረስ ይባላሉ። 

እንደተጠቀሰው ወልቃይት ዛሬ የተካለለው በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ አስተዳደር ሥር ነው። ለመሆኑ ወልቃይትና ትግራይ በነበረ ታሪካቸው ምንና ምን ናቸው?

 ከ1966 ዓ.ም. በፊት የትግራይ ጠቅላይ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን መለስካቸው አምሃ አነጋግሯቸዋል። ሙሉውን ዝርዝር ለማዳመጥ፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ። 

"የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው" ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም
Listen:
Received on Tue Mar 01 2016 - 18:34:24 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved