Mereja.com: የወልቃይት ጠገዴ እናቶች የሕወሓትን ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በበርበሬ ብጥብጥ መማረክ ችለዋል፡፡

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 25 Mar 2016 00:50:35 +0100

የወልቃይት ጠገዴ እናቶች የሕወሓትን ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በበርበሬ ብጥብጥ መማረክ ችለዋል፡፡

ወልቃይት ጠገዴ የዛሬ ውሎ (መጋቢት 15 ቀን 2008) By Muluken tesfaw

ከ400 በላይ የሚሆኑ የዳንሻ እናቶች ልጆቻችንና ባሎቻችን መልሱ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ፡፡ የትግራይ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በጠመንጃ ከበባቸው፡፡ የወልቃይት እናቶች ጣሊያን ላይ እንዳደረጉት ሁሉ በርበሬ እየበጠበጡ በዐይናቸው ላይ ደፉባቸው፡፡ መሣሪያቸውንም ማረኳቸው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ እናቶች የሕወሓትን ሽምቅ ተዋጊ ኃይል በበርበሬ ብጥብጥ መማረክ ችለዋል፡፡

———-

የዳንሻና የጠገዴ ወጣቶች ጥገኝነት በሶሮቃ ጠይቀዋል (የሚያስቅ ግን ደግሞ እውነት)፡፡ በቃ አንድ አገር ላይ እየኖርን አይደለንም ማለት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ግጨው አካባቢ በነበረው የአርማጭሆና የሕወሓት ውጊያ ምርኮ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ በዚህ ዓመት ነገሩ አድጎ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በተወለዱበት አካባቢ መኖር አልችል ብለው የሶሮቃ ወንዝን ተሻግረው ሶሮቃ ከተማ ላይ የአማራን መንግሥት ጥገኝነት ጠይቀው በኬንዳ መኖር ጀምረዋል (የሚያሳዝን እውነት)፡፡ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በየሠዓቱ እየጨመረ ነው አሉ፡፡ አሁንም ከአብራጅራና አብደራፊ የሚደርሱ ብዙ ወጣቶች አሉ፡፡ የጠገዴና (ጠገዴ ከሁለት መሆኑን ልብ ይሏል) የአርማጭሆ ወጣቶች የጀግና አቀባብ አድርገውላቸዋል፡፡

—-

አቶ ሊላይ ብርሀኔን በተመለከተ ያለ አዲስ መረጃ

ሁለት የሕወሓት ታጣቂዎች ጠልፈውት ሳለ ሽጉጥ መያዙን ስላልተገነዘቡ መኪና ውስጥ ይዘውት ገቡ፡፡ ነገር ግን እንደሚገድሉት አስቀድሞ የተገነዘበው ሊላይ ሁለቱንም እንደገደላቸውና በመጨረሻም ሌላ ወታደር እንደገደለው የሚገልጽ አዲስ ወሬ መጥቷል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወደ መቀሌ ባዶ ስድስት ተወስዷል የሚሉም አሉ፡፡ ሁለቱም ወሬዎች በሰፊው እየተነገሩ ያሉ ቢሆንም ግልጽ የሆነ የለም፡፡

——–

የጳጳሳቱ የእነ አባ ኤልሳ ምክክር የጊዜ ገደቡ ነገ ነው፡፡ ነገ የታሰሩት በሙሉ ካልተፈቱ መንገድ ይዘጋል፡፡

——-

ከአቸፈር፣ ከዳሞት፣ ከቋሪት፣ ከደብረ ታቦር፣ ከጋይንት፣ ከበለሳ፣ ከዋግና ከጎባ ላፍቶ ወደ ጠገዴና ወልቃይት የሚሔዱ ሰዎች መበርከታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ መውሰድ አለበት፡፡ መላው ኢትዮጵያዊ እንደ ኦሮሚያው ሁሉ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ ማውገዝ አለበት፡፡

—-

ይህ በዚህ እንዳለ በመተከል ቡለን ወረዳ ኤጳር ቀበሌ አሰቃቂ ወንጀል አቶ እንየው በተባለ የአማራ ተወላጅ ግለሰብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ በግለሰቡ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ነገር ለአንባቢ ስለማይመች ልዘለው ግድ ብሎኛል፡፡

ቤኒሻንጉል እስከ መቼ የብሔሮች እስር ቤት ሆና እንደምትቀጥል አላውቅም፡፡

Received on Thu Mar 24 2016 - 19:50:36 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved