Zehabesha.com: ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት የቀረበ ባለ 9 ነጥብ አቤቱታ | ተሰርቆ የወጣ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Thu, 1 Sep 2016 18:31:20 +0200

ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት የቀረበ ባለ 9 ነጥብ አቤቱታ | ተሰርቆ የወጣ

eprdf
ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት 9 ነጥብ ያለው አቤቱታ በደብዳቤ አቅርበዋል:: ይህ ምስጢራዊ አቤቱታን የውስጥ አርበኞች ለዘ-ሐበሻ እንዲደርስ አድርገዋል:: ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ ያንብቡት::

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም

ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት የቀረበ አቤቱታ

1. አማራ ክልል ላይ መንግስትን የሚቃወመው ሕዝብ ብዛቱ ምን ያክላል ለሚለው የሚሰጠው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ትዕዛዝ ይዞታ የየሚተረጉም ይሆናል፡፡ በእኔ አመለካከት ከ90% በላይ ሕዝብ ይቃወማል፡፡
በዚህ ሕዝብ ላይ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስድ ማዘዝ ጂኖሳይድ አይሆንም ወይ የሚለው ጥያቄዬ እንዲመለስልኝ እፈልጋለሁ፡፡
2. እንደምናየው የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳዘዙት እርምጃ አልወሰዱም፡፡ ማስረጃው እስካሁንም ድረስ ተቃውሞው እንደቀጠለ ሆኖ የፀጥታ ኃይሉ ከዚህ በፊት ከሚወስደው የተለየ እርምጃ እንደወሰደ አለመሰማቱ ነው፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መመሪያ ለመቀበል ገሸሽ ማለት ሥጋት የለውም ወይ?
3. ጠቅላይሚንስትሩ አጠቃላይ ሕዝብ ተገልብጦ የሚያሰማውን ተቃውሞ ለወጣቶች ብቻ መስጠቱ ተገቢ ነው ወይ? ማስረጃ የጎንደር፣ የባህር ዳር እና የማርቆስ ሕዝብ ቤቱን የዘጋው ወጣት ልጆቻቸው አስገድዶአቸው አይደለም፡፡
4. መንግስት ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ጋር የሚያጣላውን ድርጊቶች ለምን ይፈጽማል?

ማስረጃ፦ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤቶች ፈረሳ

ሀ.. ሕገ ወጥና ሕጋዊ መካከል ሰነድ አልባ ቤቶች የሚለውን የፈጠረው መንግስት ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዕረፍት በፊት ሕገወጥ ይዞታወችን በሙሉ በትንሽ የሊዝ ዋጋ ሕጋዊ እንደሚያደርግ ለሕዝቡ ገልጾ ነበር እንዲያውም የወቅቱ ጥያቄ በሊዝ ሕጋዊ መደረጉን አንቀበልም የሚል ነበረ፡፡ ያንጊዜ ከነበረው ከክቡር አቶ መኩሪያ መሥሪያ ቤት የተሠራጨ የሊዙን ከአፈጻጸም የሚያትት ሃያ ገጽ ያለው ብሮሸር ተበትኖ ነበር፡፡ አሁንም በሕዝቡ እጅ ይገኛል፡፡
ለ. መንግስት በእነዚህ በፈረሱ መንደሮች ከፍተኛ ኢንቨስት አከናውኗል፡፡
መብራት፣ ውኃ፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛዎችን፣ መንገዶችንና ሌሎችን የሚያካትት ነው፡፡
ሐ. ዘጎች ቤታቸው ሕጋዊ ይደረግላችኋል በሚል ለኮንደሚኒዬም ቤት እንዳይመዘገቡና እንዳይቆጥቡ በመንግስት መመሪያ ተከልክለዋል፡፡መ.በአዲስ አበባ ከተማ ሃያ ሺ ቤት ሲፈርስ በመንግስት ስሌት አንድ ቤት
አምስት አባላት ስለሚኖሩት 100.000 ሕዝብ ተፈናቅሏል

ውጤት፦ ሃያ ሺ ቤት መፍረሱ በአገራችን ማህበራዊ ኑሮ ስሌት የአንዱ ጥቃት በትንሹ በሁለት መቶ ሰዎች ላይ ቀጥተኛ ቁስል ያደርሳል፡፡ የወንዱ ዘመዶች፣ የሚስቱ ዘመዶች እና ጓደኞቻቸውን ያካትታል፡፡ ሃያ ሺ ሰው በሁለት መቶ ሲባዛ አራት ሚሊዬን ሕዝብ በአንድ ላይ ያቆስላል፡፡ አራት ሚሊዬን ሰው በቀን አንዳንድ ሰው ከመንግስት ቢያስኮበልል በየቀኑ አራት
ሚሊዬን እየካደ አገር ሁሉ ይገለበጣል፡፡

5. በወልቃይት ጉዳይ መላው የአማራ ክልል እየታመሰ መንንግስት የወልቃይትን ጥያቄ ትግራይ ክልል እንዲፈታ መወሰኑ ትክክል ነው ወይ?
6. በወልቃይት ምክንያት በአማራ ክልል ያለውን ተቃውሞ በጠመንጃ አፈ ሙዝ ለማንበርከክ ጦርነት በማወጅ የወልቃይትን ጉዳይ ለትግራይ ክልል መስጠት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ለሕወሀት የሚሠሩ አያስመስላቸውም ወይ?
7. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችን ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን በመካድ የሥራ ማጣት ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ አድርጎ መቅረባቸው ትክክል ነው ወይ? እስካሁን ድረስ ሥራ አጥተናል በሚል አንድም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው አያውቁም፡፡
8. የወልቃይት ጥያቄ የአገር ባለቤትነት ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን በአማራ ሕዝብና በትግራይ ሕዝብ መካከል ለዘላለም የማይታረቅ ግጭት ምክንያት ሆኖ እንደሚዘልቅ መንግስት መመልከት አለመቻሉ የመንግስትን ጠባብነት አያሳይም ወይ?

9. በመንግስት ሚዲያዎች ላይ ይህ ነው የማይባል የመንግስት በጎ ሥራ እየተሰበከ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃዋሚዎች የሚሰብኩት ሕዝቡን እንዳሳሳተ ማማረር የፕሮፓጋንዳ ሽንፈትን አያሳይም ወይ?

በእነዚህ ጥያቄዎች በመጀመሪያ ደረጃ ለራስ ህሊና ታማኝ በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ለአገር ሰላም ሲባል በሦስተኛ ደረጃ በህሊናችን አለቃ በእግዚአብሔር ፍርሃት ተገቢ ምላሽ እንድትሰጡን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ መኖር የምንችለው አገር ስትኖር በመሆኑ አሁንም መንግስ ውሳኔዎቹን በድጋሚ እንዲያያቸው በትልቅ ትህትና እናመለክታለን፡፡

Received on Thu Sep 01 2016 - 11:10:25 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved