ይህን ነገር ስፅፍላቸው አይኔ ደም እምባ እያለቀሰ እንደሆነ ተረዱኝ፡፡
ከሚኪያስ ሲመዲሳ
የቂልንጦ እስር ቤት እስረኞችን ፍርድ ቤት ከሚያመላልስ ከአንዱ ወዳጄ በቀጥታ የሰማሁትን ልንገራችሁ፡፡
“ዓርብ ማታ የማናውቀው አንዱ ትግርኛ ተናጋሪ መጣና ለተወሰኑ ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ሄደ፡፡ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ እኔ የማውቃቸው የኦሮሞ ፖሊሶች ከተመደቡበት ቦታ ተቀይረው ወደ ሌላ ከእስር ቤቱ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዱ፡፡ የእስር ቤቱ ወሳኝ የጥበቃ ቦታዎችና ማማዎች እንዳለ በአጋዚዎች እንዲሸፈን ተደረገ፡፡ እኔም ከሩቅ ከእስር ቤቱ ጥበቃ ውጭ በቅርብ ርቃት ላይ አከባቢውን ዱላ ብቻ ይዤ እንዲቃኝ ተመደብኩ፡፡ ዓርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢ፤ በእስር ቤቱ ውስጥ አደጋ ሊፈጠር ስለሚችል ሁሉም የእስር ቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ የሚል ትዕዛዝ ሰማን፡፡ ነገሩ ከወትሮው አዲስ ሆኖብን ግራ ቢገባንም ትዕዛዙን ለምን እንዴት ብለን እንኳን የመጠየቂያ እድል ስላልነበረን ተቀብላን ቅዳሜ ጠዋት ደረሰ፡፡
አራት ሰዓት ሊሆን አካባቢ ትንሽ ግር ግርና ተኩስ ተጀመረ፡፡ በዚያን ሰዓት ምንም የእሳት ጭስም ሆነ ነበልባል አይታይም ነበር፡፡ እኔ ከሩቅ ሆኜ መንገደኞችን ከመከልከል ውጪ ጠጋ ብዬ ሁኔታውን ለማጤን እድሉ አልነበረኝም ነበር፡፡ ትንሽ እየቆየ ሲሄድ ተኩሱ በረታ! አሁን የእሳት ጪስ መታየት ጀመረ፡፡ ከጥበቃ ማማው ላይ የነበሩ አጋዚዎች ወደታች በቀጥታ ስተኩሱ አያለው፡፡ ነገሩ ምንድነው ብዬ ጠጋ ማላት ጀመርኩ፡፡ አሁን ዕሳት እጅጉን እየነደደ መጣ፡፡ ቤት ውስጥ የነበሩ እስረኞች ራሳቸውን ለማዳንና ወደ ውጪ ለመውጣት መታገል ጀመሩ፡፡ ቃጠሎ በነበረበት አካባቢ በአብዘኛ ሁሉም እስረኞች በሚባል ደረጃ ከግቢ ሳይሆን ከእስር ቤቱ ውስጥ ወጥተው ተመልሰው እሳቱን ለማጥፋት ስረባረቡ በአይኔ ተመልክቻለው፡፡
ትንሽ ቆይቶ በፍፁም ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ አዲስ ነገር ማየት ጀመርኩ፡፡ እሳቱን እያጠፉ ባሉ እስራኞች ላይ ካላይና ከታች አጋዚዎች የጥይት እሩምታ ማዝነቡ ጀመሩ፡፡ እውነት ለመናገር አንድም እስረኛ ለማምለጥ ሙከራ ያደረገ የልም፡፡ በቃ ብዙ እስረኞች በጥይ ተመተው መሬት ላይ ሲወድቁ አየሁ፡፡ ገሚሶቹ ጓደኞቻቸው በጥይት ተመተውና መሬት ላይ ሲወድቁ ባዩ ጊዜ እራሳቸውን ለማዳን ተመልሶ ወደ እሳቱ ውስጥ በድንጋጤ የገቡም ብዙ ናቸው፡፡ ሌሎቹ በግቢው ውስጥ ከጥይቱ እሩምታ ለመሸሽ ወዲያና ወዲህ ሲሉ የተገደሉ ናቸው፡፡ እንዳልኩት በአብዛኛው የሞቱት እሳቱን እያጠፉ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የመጡት በጣም ቆይተው ብዙ ሰው አልቆ በአንቡላን ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከተጀመረ በኋላ ነው፡፡ በኔ በኩል የሟቾች ቁጥር 20ና ሰላሳ እንደተባለ ሳይሆን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በአብዛኛው የጥይቱ ሰለባ የሆኑት በዋህነት እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡ ምስክኑ እስረኞች ናቸው፡፡ በሆነው ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ በእውነት ምን እየተደረገ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም በማለት በምሬት ዛሬ ከነጋ አጫውተውኛል”፡፡
ይህ ወዳጄ ስለነ በቀለ ገርባ ጠይቄውት የነገረኝ ነገር ቢኖር…እንደነ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ ትልልቅ የፖለቲካ እስረኞች ከሌሎች ራቅ ብለው በብሎኬት የተሰራ ልዩ እስር ቤት ውስጥ ስለሚታሰሩ ለአደጋዉ ተጋላጭ የሚሆኑ አይመስለኝም ሲል መልሶልኛል፡፡
ያም ሆነ ይህ ጎበዝ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያለኸው የሀገሬ ሰው አሁን በግልፅ ወያኔ ሙሉ ጦርነት አውጆብናል፡፡ ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለን ትግላችንን ያዝ ለቀቅ እያደርግን ቢንመጣም ነገሩ እየባሰበት መጥቷል፡፡ ስለዚህ በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ወጣቱ በተናጠልና በተበታተነ ሁኔታ ዘግናኝ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት አስተባባሪዎች አፀፈው በተደራጀና በተቀዳጀ ሁኔታ ምን መሆን እንዳለበት በአስቸኳይ ተወያይታችሁ ለህዝብ እንዲታሳውቁ በተሰው ወገኖቻችን ስም አደራ እላለሁ፡፡
ድል ለጭቁኑ ህዝብ ሞት ለወያኔ!!!