Goolgule.com: የኢኮኖሚ አድማ! በጎንደርና ባህርዳር ነጋዴዎች ግብር መክፈል አቁመዋል

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 7 Sep 2016 16:34:23 +0200

የኢኮኖሚ አድማ!

በጎንደርና ባህርዳር ነጋዴዎች ግብር መክፈል አቁመዋል
ቡራዩ

#OromoProtests  አስተባባሪዎች በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት በኢኮኖሚ ላይ ያተኮረው የገበያ ማቆም አድማ እየተካሄደ ነው፡፡ በፎቶዎቹ ላይ እንደሚታዩት ከንጋት ጀምሮ የአምቦ አካባቢ ከተማ፣ ሻሸመኔ አዋሾ ክፍለ ከተማ፤ አሳሳ፣ ጉደርና ከተሞች ከነገበያቸው ባዶ ሆነዋል፡፡ ዓድማው በሌሎችም ከተሞች ላይ ሲካህይድ የዋለ ሲሆን በውጤቱም የህወሃትን የገቢ ኮሮጆ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳው ይገመታል፡፡

ከአስተባባሪዎቹ የተሰጠውና እስከ መስከረም 2 የሚዘልቀው ማሳሰቢያ እንዲህ ይነበባል፤

ማሳሰቢያ: የገበያ ማቆም አድማ በመላው ኦሮሚያ ነገ ጳግሜን 1 እንደሚጀምር አስቀድመን መግለጻችን ይታወቃል፡፡ ይህ አድማ እስከ መስከረም ሁለት ይቀጥላል። በዚህ አድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አቀናጆች አስታውቀዋል። የመኪና ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ይህንኑ አውቀው ይህን የአድማ ወቅት በማክበር ለህዝብ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ እና ንብረታቸውንም ከውድመት እንዲያድኑ ደግመን እናሳስባለን። (ፎቶ፡ ከጃዋር መሐመድ፣ ከጸጋዬ አራርሳና ከሌላ ግለሰብ ፌስቡክ ገጽ የተገኙ)

በሌሎች ከተማዎች የመረጃ አለመድረስ እንዳለ የጠቆሙ አንድ አስተያየት ሰጪ ይህንን ብለዋል:

“�በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልሎች ተቃውሞው በተሳካ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ደውዬ ያነጋገርኳቸው ሰዎች ገልፀውልኛል ነገር ግን አንዳንድ አከባቢዎች ጉዳዩን ካለመስማት ይሁን? ወይም ለጥሪው ምላሽ ለመስጠት አለመፈለግ? እንደወትሮው ሁሉ የእለት ተለት እንቅስቃሴያቸውን እየከወኑ ነው። ለምሳሌ ወለጋ ሲቡ ሲሬ ፣ ጅማ ፣ አሰላ፣ . . . በነዚህ ቦታዎች ላይ ሌላውን ማስተማር የሚችል ጥሩ መቀጣጫ እርምጃ መወሰድ አለበት። ዛሬ ጥዋት አንድ ባለ ሆቴል ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ገና በሩን ከፍቶ ሰዎች ማስተናገድ ሊጀምር ሲል ስልክ ደውለው ምን እንዳሉት ባላውቅም በሩን በሰከንዶች ፍጥነት ዘግቶ ከአከባቢው ጠፍቷል! ህዝብ ሲተባበር ሁሉም ይፈራዋል።”

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም ማለታቸውንና ላለፉት ሁለት ወራት ገቢዎች ቢሮ ግብር እንዳልሰበሰበ ሙሉቀን ተስፋው በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ አስታውቋል ከዚህ ጋር ተያይዞ የ#AmharaResistance አስተባባሪዎች ሕዝቡ ግብር አለመክፈሉን መቀጠል እንዳለበት ያሳስባሉ – እንዲህ ይነበባል:

“በጎንደር፣ በባህርዳር፤ በደብረ ማርቆስ እና ተጋድሎው እየተስፋፋባቸው ባሉ አካበቢዎች ያሉ ነጋዴዎች ግብር አንከፍል አሉ፡፡

“የመንግስት ባለስልጣናት የተጨማሪ እሴት ታክስ ለገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በየወሩ የገቢ ግብር ሪፖርት ማቅረብ የሚጠብቅባቸው ቢሆንም እስካሁን ላለፉት ሁለት ወራት የገቢ ግብር ያቀረበ ነጋዴ አልተገኝም፡፡

“በአሁኑ ስዓት አገልግሎቶት ሰጭዎች ባቆሙበት ስርዓት የመንግስት ፋይናንስ ላለፉት ሁለት ወራት በጎንደር በዚህ ወር ደግሞ በባህር ዳር ያሉ ነጋዴዎች ከመንግስት አካላት ግብር እንዲከፍሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለወንድሞቻችን ነፍስ መግደያ የጥይት መግዣ አናዋጣም፡፡ አሁን ላለው ስርዓትም እውቅና አንሰጥም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ላላፉት ሁለት ወራት ገቢዎች ምንም ግብር አልሰበሰበም!! የዐማራ ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም ማለቱን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው!!”

oromo cities

አምቦ

አምቦ

አዋሾ ክፍለከተማ ሻሸመኔ

አዋሾ ክፍለከተማ ሻሸመኔ

አዋሾ

አዋሾ

አሳሳ

አሳሳ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

አሳሳ ገበያ

ጉደር

ጉደር

ጉደር

ጉደር

ነቀምት

ነቀምት

ዶዶላ አርሲ

ዶዶላ አርሲ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

አወዳይ

ሻሸመኔ

ሻሸመኔ

city oromia

ሮቢ ባሌ

ሮቢ ባሌ

ቡራዩ

ቡራዩ

ቡራዩ

ቡራዩ

oromiacity1 oromiacity2 oromiacity3 shashenene o

 
Received on Wed Sep 07 2016 - 09:13:28 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved