Ethsat.com: የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ቀውስ አስመልክቶ ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 27 Sep 2016 01:25:46 +0200

የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ቀውስ አስመልክቶ ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009)

September 26, 2016

Watch these News:

ESAT DC Morning News Mon 26 Sep 2016

http://video.ethsat.com/?p=28789

ESAT Daily News Amsterdam September 26, 2016

 

በኦሮሚያና አማራ ክልል እየተከሰተ ባለው ህዝባዊ እምቢተኝነትና እሱን ተከትሎ የመጣው አለመረጋጋት በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ላይ ስጋት መፍጠሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሃላፊ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ገለጹ። ችግሩ በሚፈታበት ሁኔታ ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር መነጋገራቸውንም የአሜሪካን አቋምን በሚተነትነው ርዕሰ አንቀጽ አስፍረዋል።

ኒውዮርክ እየተደረገ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሃላፊ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ-ግሬንፊልድ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ያለው ዕርምጃ እጅግ ከባድ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተቃዋዋሚዎች ጋር የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ሲያበረታቱ እንደነበር የገለጹት ቶማስ-ግሪንፊልድ፣ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት እንዲኖር፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲያንሰራሩ፣ በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱና በተመሳሳይ ጉዳዮች ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ላይ መነጋገራቸውን አመልክተዋል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው አለመረጋጋት ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል እንደሚረዳ፣ የኢትዮጵያ መንግስትም ችግሮቹ ካልተፈቱ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እየተባባሰ ሄዶ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል እንደሚገነዘቡ ባለስልጣኗ መናገራቸው ተመልክቷል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ሊሳተፉ ከመጡት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በጎንዮሽ ተገናኘተው በጉዳዩ ላይ እንደተወያዩ የገለጹት ሊንዳ ቶማስ-ግሬንፊልድ፣ የአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት ችግሩን በጥልቀት መርምሮ ዕልባት እንዲሰጠው እንዳበረታቷቸው መናገራቸውን ገልጸዋል።

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰተ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በቅርቡ ዕልባት ካላገኘ ወደ ከፋ ደረጃ ሊሻገር እንደሚችል ሚስ ሊንዳ-ቶማስ ግሪን ፊልድ ማሳሰባቸው ተመልክቷል።

ከሶስት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተቃዋሚዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው አደገኛ እርምጃ መንግስታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ማሣሰቡንና  በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ  መጠየቃቸውን በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛና የፕሬዚዳንት ኦባማ ካቢኔ አባል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር በጁባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

የአሜሪካ መንግስት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ሲገልጽ ቢቆይም፣ ስለጉዳዩ አሳሳቢነት በተደጋጋሚ ሲናገር ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተሰናባች አምባሳደር ፓትሪሽያ ሀስላክ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ያለህግ እንደሚታሰሩና የኤምባሲው ሠራተኞች ጭምር ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነገር እንደሚፈሩ መናገራቸው አይዘነጋም።

ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከወራት በፊት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በገለልተኛ አለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን ማጣራት እንዲደረግበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት ቢጠይቅም በኢትዮጵያ መንግስት እምቢተኝነት ሳይሳካ መቅረቱን መዘገባችን ይታወሳል።

*********************************************************************************

በኢትዮጵያ የባለአደራ መንግስት እንዲቋቋም ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት (መስከረም 16 ፥ 2009)

September 26, 2016

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ፣ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ቀውስ ለመሻገር ባለአደራ መንግስት እንዲቋቋም ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ጥሪ አቀረብ።

በተለያየ መንገድ ከሃገሪቱ የተዘረፈውን ገንዘብ በተመለከተም የሂሳብና የህግ አዋቂዎች የሚሳተፉበት የምርመራ ስራ እንዲካሄድና የውጭ አማካሪዎችም ሂደቱን እንዲያግዙ የመፍትሄ ሃሳብ አቅርበዋል።

ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ይህንን ጥሪ ያደረጉት ዛሬ ሰኞ መስከረም 16 ፥ 2009 ባሰራጩት ባለ11 ገፅ ጹሁፍ ነው።

“የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት” በሚል ርዕስ ባሰራጩት መልዕክት የትግራይ ህዝብ በህወሃት ሳቢያ ከፍተኛ መከራ እንደተደቀነበት አስረድተው፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሰለፍ አደጋውን እንዲሻገረው ጥሪ አቅርበዋል።

“የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኗል፣ ይህ የሚያከራክር አይመስለኝም” ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ከ25 አመታት በላይ በጠመንጃ ጉልበትና በሲአይኤ (CIA) ድጋፍ ሰንጎ የገዛን ቡድድን በቃህ ቢባል አይደንቀኝም” በማለት ጽሁፋቸውን ቀጥለዋል።

ስርዓቱ እንዴት ይውረድ የሚለውን ጥያቄ አስከትለው በዚህ ረገድ አሉ ያሏቸውን ያልጠሩ አመለካከቶች በዝርዝር ተመልክተዋል።

“የወያኔ ሎሌዎች በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሱትንም የቃጡበትን ከባድ አደጋ በጥልቀት ስለተገነዘብኩ የምችለውን ያህል ለማስተካከል ቆርጫለሁ ያሉት ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም፣ ትግራይ በሁለት ሆን ተብሎ ወያኔ ጠላት ባደረጋቸው ህዝቦች መሃከል ተጥዶ እንደገና ዳቦ እሳት እስኪቀጣጠልበት እየተጠበቀ ነው” በማለት የችግሩን ስፋትና አሳሳቢነት ዘርዝረው ሃገሪቱ ላለችበት ጥልቅ ችግር መፍትሄ ያሉትን የባለአደራ መንግስት ሃሳብ በዝርዝር አቅርበዋል።

በዚህም ነጻ የተወካዮች ም/ቤት እንዲቋቋም፣ በዚህ ም/ቤት ተቆጣጣሪነትም ለሁለት አመታት የሚቆይ የባለአደራ መንግስት እንዲቋቋም የመነሻ ሃሳብ አቅርበዋል። ከሃገሪቱ የተዘረፈውን ገንዘብ በተመለከተም የህወሃት ባለስልጣናት ንብረት በህግና በሂሳብ አዋቂዎች እንደመረመር፣ በሂደቱም የአለም ባንክና የተባበሩት መንግስታት እንዲሁም የምዕራብ መንግስታት አማካሪዎች እንዲሳተፉበት ጠይቀዋል።

ተጣርቶ የተገኘው ሃብትና ለሃገሪቱ ልማት፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና ለሟች ቤተሰቦች እንዲውል ፕ/ር መስፍን የመፍትሄ ሃሳብ አቅርበዋል።

እነርሱ በለቀቁ ማግስት በሚካሄደው የመጀመሪያው ምርጫ የህወሃት መሪዎች ሆነ ካድሬዎች እንዳይሳተፉ በህግ ገደብ እንዲጣልባቸው ባለ 11 ገጽ ጽሁፋቸው፣ ፕ/ር መስፍን የመፍትሄ ሃሳብ አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምና ሌሎች ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለደርግ መንግስት በተመሳሳይ የአደራ መንግስት ጥያቄ ማቅረባቸው ሲቃወም፣ ስርዓቱ አልቀበልም ማለቱን ተከትሎ በወራት ልዩነት ከስልጣኑ መባረሩ አይዘነጋም።

 
Received on Mon Sep 26 2016 - 18:04:50 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved