ዛሬ ጨለሞ ዋለ። ዛሬ አገር ማቅ ለበሰች። ዛሬ የሆነውን ማመን ይከብዳል። ቄጤማና ቅጠል ይዘው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተረሸኑ። “Down! Down! Woyane … Down! Down TPLF! …” በማለት ቁጣውን የገለጸ ሕዝብ እገዛሃለሁ በሚለው የትግራይ ህዝብ ተገንጣይ ቡድን (በህወሃት) ተጨፈጨፈ። ከአየርና ከምድር ጭስና ጥይት የተረጨበት ህዝብ፣ የሚገባበት ጠፍቶት የውሃ ራት ሆነ። ሞተ። ቆሰለ። በውሃ ተበላ።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሚባለው የወንበዴው ቡድን መሪ መለስ ሞት በድንገት እንደ ቡሽ ክዳን አፈናጥሮ ሲወስደው ጥቁር ለበሶ ሳግ እየተናነቀው ዜና ያወጀው ተመስገን በየነ፣ ዛሬ ነጭ በነጭ ለብሶ አኻዝ ባይጠቅስም የሰው ህይወት ማለፉን የተናገረው “ሰፊውና የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ” በማለት ነበር።
ተመስገን ከጌታቸው የተላከለትን ሰዎች “በመረጋገጥ” ሞታቸውን ሲተፋ ቢያመሽም ህወሃትና ወኪሎቻቸው የዘነጉት ነገር ቢኖር የኢሬቻ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ዛሬ አይደለም፤ እስካሁን በተደረገው የበዓሉ አከባበርም ሁከት ሲነሳና ሰዎች በመረጋገት ሲሞቱ አልተሰማም፡፡
ብዙዎች እንዳሉትና፣ በማህበራዊ ገጾች እንደታየው ከኖረው ሃዘን ጋር ተዳምሮ የዛሬው ሃዘን በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር መጠናቀቁን ነው፡፡
የማህበራዊ ድረ ገጾች ምስል አስደግፈው እንዳሰራጩት ዜናና የውጭ መገናኛዎች እንዳሉት ቢሾፍቱ የኢሬቻን በአል ለማክበር የተሰባሰቡት ዜጎች ብዛት እስከ አራት ሚሊዮን ተገምቷል። ቢቢሲ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሲል ሌሎች ከዚያም ያስበልጡታል።
እንግዲህ እዚህ ህዝብ መሃል ነበር መርዝ የተተኮሰው። ጭስ የተተኮሰው። ህዝብ አየር አጥቶ እንዲታፈን የተፈረደው። ከዚያም በላይ ከባድ መሳሪያ ሲተኮስ የተቀረጹት ፊልሞች አረጋግጠዋል። ታንክ ሲጠቀሙም በምስል ተይዟል። በአየር ላይም ሄሊኮፕተር ተባባሪ ነበር።
ይህ ሁሉ የመሳሪያ አይነት የተሰለፈው ለወገን መሆኑ አገርን በድፍን አሳዝኗል። በዚህ ሁሉ ዝግጅት በተካሄደ የጅምላ ጭፍጨፋ ንጹሃን ዜጎች ሞቱ። ዜናው ከተሰማበት ደቂቃ ጀምሮ የሚወጡት መረጃዎች አስደንጋጭ ናቸው። ለጎልጉል መረጃ የሰጡ እንዳሉት “ሕዝብ ሲቃወም ዝም ቢሉ ምን ችግር ነበረው? ሲቃወም ውሎ ሲመሽ ወደቤቱ ይሄዳል!” እኚህ ሰው እንዳሉት በዓሉ በሚካሄድበት ስፍራ ህወሃትን የሚያሰጋው ነገር የለም። ቀድሞውኑ ህዝቡ ተከቦ ነበር። የተከበበና ከመንገድ ጀምሮ ተልብጦ ሲፈተሸ የዋል ህዝብ ምንም አደጋ ሊያስከትል እንደማይችል የታወቀ ነው። “ሲጀመር ፍርሃቻ የያዘው ህወሃት ህዝብ ሲሰበሰብ ስለሚታመም ከበሽታው በመነጨ ምላጭ ስቦ ህዝብን ረሸነ። ጨፈጨፈ። አቆሰለ። ይህ የማይሽር ጠባሳ በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዋጋ ያስከፍላል። ይቅርታ የለውም። አሁን የይቅርታን ገመድ በጠሷት። አለቀ። ካሁን በኋላ …”
እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ጎረምሶች … በያይነቱ በህወሃት መጨፍጭፋቸውን ህዝቡን አገንፍሎታል። በስፋት እንደሚባለው “አሁን ጊዜው ወያኔን በምትችለው ሁሉ ታገለው። ቦታ አትምረጥ፣ ጊዜ አትምረጥ … ወዘተ” የሚሉ ናቸው። የጅምላ ጭፍጨፋውን ተከተሎ አምቦ ህዝብ ቁጣውን አሰምቷል። በይፋ ባይነገርም እዚያም የህወሃት አንጋቾች ነፍስ አጥፍተዋል። ህዝቡም ንብረት አውድሟል። በሌላ በኩል ከቢሾፍቱ ወደደቡብ የሚወስደው መንገድ በበርካታ ቦታዎች ተዘግቷል፡፡
በጥልቀት መታደስ እያለ ሲፎክር የነበረው ህወሃት አመራሮችን ቀይሬአለሁ ብሎን ነበር፡፡ በመለስ ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ንጹሃንን የጨፈጨፈው ወንጀለኛው ወርቅነህ ገበየሁን የኦሮሞ ህዝብ መሪ አድርጎ ከሾመ በኋላ የዛሬውን ዓይነት ጭፍጨፋ በማድረግ ወርቅነህ ለራሱና ለለማ መገርሣ “ሹመት ያዳብር” የሚያሰኝ ታማኝነቱን አሳይቷል፡፡
ህወሃት ጠርንፎ የያዛት አገራችን ጉዳይ አሳሳቢ ከሚባልበት ደረጃ አልፏል፡፡ በርካታ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ሰላማዊ ሰዎች በዛሬው ዕለት ጠአቅጣጫ ለውጥ ሲያደርጉና ሲያሰሙ ማድመጥ የወንበዴው ቡድን ህወሃት ጉዳይ በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር ያበቃለት መሆኑን ያመላከተ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ጥቂት የሕዝብ አስተያየቶችን ከዚህ በታች አቅርበናል፤
በርካቶች ኢሬቻ ሊያከብሩ ወደ ሆራ ሲሄዱ እንዲህ እያሉ ነበር …
“Nuti shororkessa miti, wayyaaneen shororkessadha”
“እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፤ አሸባሪው ወያኔ ነው”
ዋሹ?
Ye Kebede Yetnayet And here is the evidence . A highly trained government commando covering his face as a terrorist. Also a heavily armored “Zilla” (a heavily armored technical vehicle recently assembled at Beshoftu Armament industry of METEC). The picture says it all- the killing was planned well in advance.
የኢሬቻን በአል እያከበሩ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ነገር እጅግ አሰቃቂ ነው። ለወትሮው ደብረዘይት/ቢሾፍቱ ከተማ ኢሬቻ በሚከበርበት ቀን፤ ወደ ሆራ በሚሄድ እና በሚመለስ ሰው ይጨናነቅ ነበር። ዛሬ ግን ከግማሽ ቀን በላይ አልቆየም። ወታደሮቹም ከየመንገዱ ያገኙትን እየደበደቡ ሲሰበስቡ ነበር። መንገዶቹ ጭር ብለዋል። ቢሾፍቱ ሆስፒታል በጣም በርካታ ህዝብ ተሰባስቧል። ግቢው ለቅሶ ቤት ነው የሚመስለው። እራሳቸውን ጥለው እያለቅሱ ወደ ሆስፒታሉ የሚሄዱ እናቶችን ማየት ይረብሻል። የሬሳ ሳጥን ይዘው የሞተባቸውን ቤተሰብ ሬሳ ለመውሰድ ሆስፒታሉ በር ላይ የሚጠብቁም አሉ።
★★★
እረፋድ ላይ ወደ ሆራ የሚሄዱና የሚመለሱ ወጣቶች እየጨፈሩ በድፍረት በሚያሰሙት ሰላማዊ ተቃውሞ ተደስቼ እና አድንቄያቸው ሳልጨርስ ነው ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው።
Addis Assefa Gonfa That is what I’M feeling…It did not have to be this way though…where is civilization?…where is common sense in all this? I don’t know why so many has to be sacrificed? So many has to be distracted? But now it looks the only way is out of this is fire with fire blood with blood…the barbaric way…the way they opted for…the only way they know….and I guess the end will be tragedy of an immense proportions… As a people Oromo in the past one year has walked the high walk with all the sacrifice to avert this … but it all fell on deaf ears… so let the *** begin
Kebede Degefu Nothing to say but I am outraged saddened no hope for political practices will work in that part of the world
Shovels must be changed to weapons, axes must be used the war they have started overhead must be reversed by all means
Bira’anuu Kabadaa Absolutely, everything has a limit! Our wish for peace and our resilience towards injustice in the name of peace fall on deaf ears and eyes! We can not go on like this everyday, our people being massacred and our heart broken.
የነሱ አሸንዳ ያለምንም ኮሽታ ይከበራል እነሱን የሚደግልፍ ሰልፍም እንደዛው ሌላው ህዝብ ግን እንደ ቅጠል ይረግፋል
አንድ ዶክተር ከቢሾፍቱ እንደተናገሩት
«ለ41 አመታት ያህል በህክምና ሙያ ውስጥ አገልግያለሁ፤ በኢትዮ―ኤርትራ ጦርነት ላይም በሃኪምነት አገልግያለሁ። በአንድ ቀን ይሄን ያህል ግድያ ሳይ ግን ይህ የመጀመሪያዬ ነው።»
We have a unique regime. They kill civilians & the call it stampede and will declare mourning days
Tsedale Lemma
Every yr, millions of #Oromo gather to celebrate #Irreecha, non have died of ‘Stampede’ until today. Heartbreaking!! #Irreechamassacre
BefeQadu Z. Hailu
People peacefully protested they don’t want cadres speak in #Irrecha and police shot teargas on them, blamed stampede.
BefeQadu Z. Hailu
#Qilinto prison caught in fire and inmates run to survive. Warders shot them and gov in #Ethiopia said people died in stampede.
Dawit T.
Too much to comprehend, too much to justify, too much to theorize, and too much to forgive. Ain’t too less to act upon it! #IrrechaMascara
Tsegaye Ararssa feeling determined.
Unfortunately, it has become increasingly more and more obvious that there is little likelihood for political end to this carnage. Regrettably, only military solutions are availing themselves. It has become abundantly clear that the matter now is going to be settled on the streets and jungles of Oromia, not on the corridors of the political class in Addis or on the diplomatic corridors of the regime’s foreign patrons. This must be the limit of politics, national and international.
ሰላማዊው ሕዝብ
የህወሃትን የበላይነት ለማስጠበቅ ደም እንዲያፈሱ ሙሉ ሥልጣን የተሰጣቸው
በታንክና በሔሊኮፕተር የተከበበው ሕዝብ ተጨፈጨፈ
የቤተሰብ እጅግ የመረረ ሐዘን
Dina Alemayehu ስለ እህቷ ይህንን አለች “ምን ልበል? ምን ላድርግ እህቴ!? ተቃጠልኩልሽ! ተንገበገብኩልሽ እህቴ!! ገና ነበር እኮ ጊዤሽ! እንዴት ልሁን?! ምን ልሁን ሰላምዬ?!! ኢህአዴግ ቀማኝ እህቴን!!!” በቀኝ የሚታዩት እናቷ ናቸው – ለርሳቸውም ዲና ይህንን አለች “እማዬ ይሄው እንደዛ ምትሳሽላት እህትሽ እንደወጣች ቀረች አቃጠለችን እኮ እግዚአብሔር ለእህቴም ለኢትዮጲያም ህዝብ ይፈርዳል”
ሲፈን ለገሰ ትዳር ከመሰረተች ገና ስድስት ወሯ ነው – ዛሬ በህወሃት ተቀጥፋለች ወንድሟ Ambo Gara Galgala ይህንን ብሏል። “ካገባች እንኳን ስድስት ወር ያልሞላት እህቴ ሲፈን ለገሰ ዛሬ ከጎኔ ተለየች። በቢሾፍቱ ሌሎች የቀመሱትን የሞት ፅዋ እሷም ተጋራች። ሃዘኔ መራር ነው ሲፎኮ ምንም የምናገርበትም አደበት የለኝም። ፈጣሪ ነፍስሽን በገነት ያኑረው!”