Ethsat.com: በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ትጥቅ ለማስፈታት ከሄዱ ወታደሮች ጋር ተዋግተው በርካታ ወታደሮችን ገደሉ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 14 Oct 2016 00:40:41 +0200

በሰሜን ጎንደር  የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ትጥቅ ለማስፈታት ከሄዱ ወታደሮች ጋር ተዋግተው በርካታ ወታደሮችን ገደሉ

ESAT DC Breaking News Thur 13 Oct 2016

http://video.ethsat.com/?p=29427

ESAT DC Morning News Thur 13 Oct 2016

http://video.ethsat.com/?p=29432

ESAT Daily News DC 13 Oct 2016

ESAT Daily News Amsterdam October 13,2016

October 13, 2016

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን የመከለከያ ጄኔራሎች፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦች፣ የልዩ ሃይል አዛዦች እና የአማራ ክልል አዛዦች ጎንደር ሲኒማ አዳራሽ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከብአዴን አመራሮች ጋር አድረገውት በነበረው ስብሰባ ፣ ህዝቡ በሰላም ትጥቁን እንዲፈታ ለማግባባት የሞከሩ ቢሆንም ፣ በስብሰባው የተሳተፉት ሰዎች ግን  “ በገንዘባቸው የገዙትን የራስ መጠበቂያ መሳሪያ አስረክቡ ብለን አንቀሰቅስም” በማለት አቋማቸውን ግልጽ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ወታደሮች ዛሬ ሃይል በመጠቀም መሳሪያ ለመቀማት ወደ አርማጭሆ  ሲሄዱ ከነጻነት ሃይሎች ከፍተኛ ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል።

በተለይ በአርማጭሆ ዶጋ በረሃ ላይ ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ቁጥራቸውን በትክክል መናገር ባይቻልም በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በውጊያው የተሳተፉ አርበኞች ገልጸዋል ። ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው የተሰማራ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በርካታ ወታደሮች መግደሉ የተዘገበለትና በአካባቢው ህዝብ ዘንድ በጀግንነቱ የሚወደሰው የነጻነት አርበኛ አበራ ጎባው በተኩስ ልውውጡ መሃል ሳይሰዋ  እንዳልቀረ እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል። ሌላው የነጻነት ተዋጊ ደጀኔ ማሩ ያለበት ሁኔታ ባይታወቅም፣ ወታደሮች ቤቱን ሰብረው ገብተው ለመፈተሽ መሞከራቸውንና  ህዝቡ ከያካባቢው መሰባሰቡን ሲያዩ ጥለው መውጣታቸውን ምንጮች አክለው ተናግረዋል።  የአካባቢው ህዝብ በወታደሮች ተከበው የነበሩትን በርካታ የነጻነት ሃይሎች መሃል ገብቶ እንዲያመልጡ መርዳቱም ታውቋል።

በአርማጭሆ በረሃዎች ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱ ሃይሎች አሉ በሚል የተንቀሳቀሰው ወታደራዊ ቡድን፣ ያልጠበቀው ጥቃት ከደረሰበት በሁዋላ የአካባቢው ህዝብ ማንኛውንም የጦር መሳሪያ እንዲያስረክብ ለማድረግ በግል እየነጠለ ጥቃት እየፈጸመ ነው።

የጦር መሳሪያ የመቀማቱ እንቅስቀሴ በሚቀጥሉት ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ በርካታ አርሶአደሮች መሳሪያችንን አናስረክብም በማለት ጫካ እየገቡ ነው። ገዢው ፓርቲ አገሪቱ በወታደራዊ እዝ ስር መውደቋን ባስታወቀ ማግስት በአማራ ክልል የሚገኝ ማንኛውንም የጦር መሳሪያ ለመቀማት ቅድሚያ ተግባሩ አድርጎታል።

በሌላ በኩል በጎንደር የአንደኛ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ተማሪዎችን የሰበሰቡት የከተማው ባለስልጣናት፣ ኢህአዴግ ባለፉት 25 አመታት አገኘሁ ያለውን ድል መናገር ሲጀምሩ ተማሪዎች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።

********************************************************************************
 
Received on Thu Oct 13 2016 - 17:19:46 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved