Mereja.com፡ አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች።

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 16 Oct 2016 01:36:00 +0200

አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች።

አምባገነኖቹና ኣዋጃቸው “ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች

እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰው በተደነገገበት የመመሪያው ክፍል፤ የህግ አስከባሪዎች የመመሪያውን ድንጋጌ ተላልፈው በተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እርምጃዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።

ክልከላዎች ሲጣሱ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ፤ በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራት ተፈፅመው ሲገኙ፤

1. ህግ አስከባሪዎች ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ፤

2 አዋጁ ተፈፃሚነቱ እስከሚያበቃበት ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆዩ የማድረግ፤

3 ተገቢውን የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ፣ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማደረግ

4 ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በማንኛውም ስአት ብርበራ የማድርግ፤ የአካባቢውን ህዘብ እና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈፀመበት ወይም ሊፈፀምበት የሚችል ንብረት መያዝ፤ወይም ንበረቱ እንዲጠበቅ ማደረግ

5 በማንኛውም ሬድዮ ቴሌቭዠን ድምፅ፣ ምስል ፎቶ ግራፍ፣ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልእክቶችን መቆጣጠር እና መገደብ ኢሳትና ኦ.ኤም.ኤን ሲያይ የተገኘ ይታሰራል

6 የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ

7 በትምህርት ተቋማት ሁከት እና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምት መውሰድ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትእዛዝ መስጠት

8 ማንኛውም የህዝብን ሰላም እና ፀጥታ ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩ እና የሚታሰቡ ሰዎችን እንዲሁም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢ እንደይገቡ፣ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ አግባብነት ያለቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።

ራስን ለመከላከል በፀጥታ ሀይልች ስለሚወሰድ እርምጃም መመሪያው ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።

ህግ አስከባሪዎች እና በድርጅት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለት ህይወታቸውን እና ንብረተቻውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረ ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።

በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣንም በመመሪያው ስንጋጌ ወጥቶለታል። መመሪያው እንደሚለው በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላት በተቋማቱ ውስውጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላሉ።

በሌሎች የመንግስት እና የግል ተቋማት አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አካላት እና ባልደረቦች በተቋማቱ ውስጥ ለመግባት እና አስፈላጊ ከሆነ ለማቆየት ይችላሉ።

ተሃድሶ እና ፍርድ ቤት ማቅረብን በተመለከተም መመሪያው ይህንን ይላል፤ 

በህግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሃድሶ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በተጠቀሰበት የአዋጁ ድንጋጌ፤ ኮማንድ ፖስቱ ለፍርድ መቅረብ ያለበትን እንዲቀርብ ያደርጋል፤
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በተፈፀሙ የሁከት እና የነውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ

የጦር መሳሪያ ሳይዝ የመንግስትም ሆነ የግለሰን ንብረት የዘረፈ እና በአቅራቢያው ለሚገኝ ፀጥታ አስከባሪ ሃይል የዘረፈውን መሳሪያ እና ንብረት፤ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን የሰጠ ፤

ከዚህ በፊት ለህገ ወጥ ተግባራት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድርግ የተሳተፈ እና ያነሰሳ፣ ሰው የገደለ፣ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ስው፤

ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን ከሰጠ እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላል እና ከባድነት ዋና ፈፃሚ እና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ፣ በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።

Source  Fana Broadcast

Received on Sat Oct 15 2016 - 18:15:04 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved