(ዘ-ሐበሻ) በዚህ ሳምንት በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በግፍ የተገደለውን ቀዘለአ ዳፈርሻ ረጋሳን ለመቅበር 100 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በሜታ ሮቢ ወረዳ ወጣ::
በ2007 ዓ.ም በተደረገ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሜታ ሮቢ ወረዳ ውስጥ 140,627 ሰዎች ይኖራሉ:: ይህም ማለት በዛሬው ዕለት ይህን ወጣት ለመቅበርና መንግስትን ለመቃወም የወጣው ሕዝብ ብዛት የወረዳው ሕዝብ ግልብጥ ብሎ ለቀብርና ቁጣውን ለመግለጽ ወጣ ለማለት ያስችላል::
በቭዲዮ ተደግፎ በተለቀቀው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቼ ሕዝብን አፍናለሁ ቢልም በሜታ ሮቢ ሕዝቡ የኦነግን እና የሜጫና ቱለማን ባንዲራ ይዞ በመውጣት ለትግራዩ መንግስት ያለውን ጥላቻና አልገዛም ባይነት አሳይቷል::