October 18, 2016
Watch these:
ESAT DC Morning News Tue 18 Oct 2016
ESAT Daily News Amsterdam October 18, 2016
http://video.ethsat.com/?p=29625ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለይ በአርሲ እና በምስራቅና ምእራብ ጉጂ ዞኖች አፈናው በእጅጉ ተጠናክሮ ቀጥሎአል። የአጋዚ ወታደሮች ወደ አካባቢው በስፋት በመሰማራት መንገድ ላይ ያገኙትን ወጣት ከማፈስ ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅት አባላትም እየታሰሩ ነው። እስር ቤቶች እየሞሉ ፣ መኖሪያ ቤቶች ወደ እስር ቤት እየተለወጡ ነው።
ከቢሾፍቱ እልቂት በሁዋላ በአካባቢው ተነስቶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ የሼክ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲ ንብረት የሆነው ዳዋ ኦኮቴ የወርቅ ማውጫ ኩባንያ ተቃጥሎ ወድሟል። ኩባንያውን ያቃጠሉትን ለመያዝ ነው የሚል ሰበብ የሚሰጡት አጋዚዎች፣ ሴት ወንድ ሳይሉ ሁሉንም በገፍ እየያዙ ማሰራቸውን ተከትሎ የሚችሉት ጨካ ውስጥ ተደብቀው እያንዳንዷን ቀን በርሃብ እያሳለፉ ነው።
አጋዚዎች በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች እየገቡ ዲሽ መነቃቀላቸውንም ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአርሲም ባለሃብቶችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና መምህራንን ማሰር የቀጠለ ሲሆን፣ የሮቤ ጄና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት መምህር ሙሐመድ ቡልቡሊ ከቤታቸው በምሽት ከተወሰዱ በሁዋላ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ታውቋል፡፡ በዚሁ ዞን በአርሲ ሮቤ ጄና ገደምሳ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ 70 ሰዎች በጅምላ የታሰሩ ሲሆን፣ አቶ ፈዮ ገለቴ እና ቃሶ ሁሴን በማንኛውም ሰአት ሊገደሉ ይችላሉ የሚል ፍርሃት መኖሩን ምንጮች ገልጸዋል፤፡
በሻሸመኔ የቢሸን ሰላም ውሃ ባለቤት የሆኑት ባለሃብቱ አቶ ተሾመ ጉዱ አጋዚዎች ወደ መኖሪያ ግቢያቸው በመሄድ ከፍተኛ ድብደባ ከፈጸሙባቸው በሁዋላ፣ ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ ነው። በከተማዋ ተደርጎ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ወጣቶች ራሳቸውን ለመከላከል ወደ መኖሪያ ግቢያቸው መግባታቸውን ተከትሎ፣ አጋዚዎች ልጆቹን በራስህ መኪና ጭነህ ወደ እስር ቤት ውሰድ ብለው ሲያዙዋቸው፣ አቶ ተሾመ “ ልጆቹ ወንድሞቼ ናቸው፣ ግቢውም የእኔ ነው “ በማለት መመለሳቸውን፣ “የጦር መሳሪያ አለህ?” ተብለው ሲጠየቁም ፣ “ህጋዊ ፈቃድ ያለው የጦር መሳሪያ አለኝ” ብለው ሲመልሱ አጋዚዎች ዱላቸውን በጭካኔ አሳርፈውባቸዋል።
የፓራዳይዝ ቫሊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለቤትን ጨምሮ ሌሎች ባለሀብቶች ወደ አዲስ አበባ ተወስደው ታስረዋል።