Satenaw.com: “የኤርትራ አብራሪዎች የጦር ጀት ይዘው ወደ መቀሌ ገቡ” የሚለው ዜና ውሸት ነው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 30 Oct 2016 13:07:13 +0100

“የኤርትራ አብራሪዎች የጦር ጀት ይዘው ወደ መቀሌ ገቡ” የሚለው ዜና ውሸት ነው

[ደርጀ ሀብተወልድ]

Watch this፡ 

ESAT Efeta Fri 28 Oct 2016

14716100_1174665025958485_139088521504213482_n“የኤርትራ አብራሪዎች የጦር ጀት ይዘው ወደ መቀሌ ገቡ” የሚለው ዜና ምንጭ የሆነው የአሶሲየትድ ፕሬሱ ፍሪላንስ ሪፖርተር ኤሊያስ መሰረት ታዬ ነው። ዜናውን ተከትሎ ኮካዎችና አይጋፎረም ከሰባት ዓመት በፊት በድረ ገጽ ላይ ከተለቀቁ የኤርትራ ጄቶች ምስል በመውሰድ ሙሉ ቀን ችርስ ሲያጋጩ ዋሉ። እኛም ፦”የለጠፋሁት ፎቶ የውሸት ነው” ብለን መረጃውን ስናሳያቸው ፎቶዋን ለወጥ አድርገው የመለማመጃ ጄት ለጠፉ። ያም ውሸት እንደኾነ ስንነግራቸው ከአል አሙዲ እርሻ ላይ ነው ያነሷትን ነው መሰል አንዲት ሚጢጢዬ የጸረ-ሰብል ተባይ መርጫ አውሮፕላን ለጠፉ።
እኛም፦ “ወሬው ሀቅ ቢሆን ኖሮ ፣እንኳን የጦር ጄት የጦር ሰገባ ቢያገኝም በፕሮፓጋንዳው አገር ይያዝልኝ የሚለው ወያኔ አርፎ አይቀመጥም ነበር። በውሸት ሙዚቃ ባትደንሱ መልካም ነው” ብለን መከርናቸው። እነሱ ግን ምክራችንን ሊሰሙ ፈቃደኛ አልሆኑም።
እነሆ ሳይውል ሳያድር የዜናው ምንጪ የሆነው አሶሲዬትድ ፕሬስ ፤ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፍሪላንስ ሪፖርተሩ የተሠራው ይህ ዜና ውሸት እንደሆነ እንደደረሰበት በመጥቀስ ለተፈጠረው ስህተት በአሜሪካ ለሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ በኢሜይል ይቅርታ መጠዬቁን የኤርትራ ፕሬስ እንደሚከተለው አስነብቦናል፦

*******************************************************************************

Eritrean Press


Apology to Eritrea 

Associated Press
by CDE


29 Oct 2016 – A reporter’s credential is revoked after he falsely reported that two Eritrean pilots defected to Ethiopia with their military jet. The article in question, from 27 October, was by an Ethiopian freelance journalist, Elias Meseret Taye (pictured), working for AP. In an email to Eritrean embassy in Washington, his employers wrote, “we cherish the trust our readers place in us to provide an accurate and vivid account of the world. On this case, the article was false and created subsequent ill-informed and damaging coverage in other media outlets and across social media.”

Received on Sun Oct 30 2016 - 08:07:13 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved