ኢሳት (ጥቅምት 22 ፥ 2009)
November 1, 2016
Watch.
ESAT DC Morning News Tue 01 Nov 2016
ESAT Daily News DC Tue 01 Nov 2016
ESAT Daily News Amsterdam November 01, 2016
http://ethsat.com/2016/11/esat-daily-news-amsterdam-november-01-2016/በአቶ ሃይለማሪያም አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተደረገው የካቢኔ ሹም ሽር በኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለውን ውጥረት እንደማይቀርፍ ተገለጸ።
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ መልክ ያደራጁትን ካቢኔ መጽደቁን ተከትሎ አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ አሁን ህወሃት እየሄደበት ያለው መንገድ በፊት ሲያደርገው ከነበረው ምንም ልዩነት የሌለው እንደሆነ ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ዶር መረራ ጉዲና ባለፈው ሳምንት ለቪኦኤ ሲናገሩ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የፖለቲካ ቀውስ ሊለወጥ የሚችለው አዲስ ምርጫ በማካሄድ እንጂ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን ባለስልጣናት ቦታ መቀያየር እንዳልሆነ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የካቢኔ ሚኒስትርነት ሹመት ባለስልጣናቱ ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው እንዲቀጥሉ ወይም ደግሞ እንዲሸጋሸጉ ተደርጓል ቢልም፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በበኩላቸው ከዚህ በፊት የነበሩትን ባለስልጣናት ማሸጋሸግ ወይም ደግሞ በአዳዲስ የኢህአዴግ አባላት መተካት የኢትዮጵያ ህዝብ አንግቦ የተነሳውን የነጻነት ጥያቄ አይመልሰውም ሲሉ ገልጸዋል።
ዶ/ር መረራ እንዳሉት ባለፈው ሳምንት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው የገዢው ፓርቲ ከስልጣን ወርዶ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ እንጂ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ባለስልጣናት እንዲቀያየሩ አይደለም ሲሉ ለቪኦኤ የእንግሊዝኛው ክፍል ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ህወሃት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው የፖሊሲ እንዲለወጥ እንጂ እንዲጠገን አይደለም ሲሉ አስረድተዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆኑት ሰለሞን ተሰማ ለዚሁ ለቪኦኤ የእንግሊዝኛ አገልግሎት እንደተናገሩት የአቶ ሃይለማሪያም መንግስት የሚያደርገው የካቢኔ ሽግሽግና ሹመት በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ የፈለገው ነጻነትን እንጂ የሰዎችን መቀያየር አይደለም ሲሉ አቶ ሰለሞን ተሰማ ለቪኦኤ አስረድተዋል።
እየሰራን ያለውን ላለፉት 25 አመታት የኢህአዴግን የስልጣን የበላይነት ለማብቃት እንጂ ጠጋግኖ እንዲቀጥል አይደለም ያሉት አቶ ሰለሞን፣ በኢህአዴግ ውስጥም ሆነ ከኢህአዴግ ውጭ ለውጥ እንፈልጋለን ማለታቸውን በቪኦኤ የእንግሊዝኛው አገልግሎት ላይ የሰፈረው ዜና ያስረዳል።
የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉን-አቀፍ የሆነ ንግግር እንዲካሄድ በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ህወሃት/ኢህአዴግ በአዲስ ካቢኔ ያካተታቸው ባለስልጣናት አብዛኞቹ የኢህአዴግ ፓርቲ አባላት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።