| Jan-Mar 09 | Apr-Jun 09 | Jul-Sept 09 | Oct-Dec 09 | Jan-May 10 | Jun-Dec 10 | Jan-May 11 | Jun-Dec 11 | Jan-May 12 |

[dehai-news] Ethsat.com: በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 16 Nov 2012 18:48:19 +0100

በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ

ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱን ጮህቱም ሰሚ ማጣቱን አንዲት የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ። ሥለችግሩ ብናነሳም የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ምን አገባችሁ በሚል መሳለቂያ ያረጉናል ሲሉም ምሬታቸውን ሲገልጹ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታይተዋል።

የዲሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈጻሚ ተቋማት ኋላፊነት በሚል ርዕስ ባጠቃላይ በሚንስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ ይህንን የተናገሩት የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ናቸው። በመንግስት የተቋቋመው የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር የተሾሙት በጠ/ሚንስትሩ አቅራቢነት በፓርላማ ሲሆን ሕዝቡ ብቻ ሣይሆን እኛም ሰሚ አጥተናል ሲሉ በሚከተለው ሁኔታ ገልጸዋል።

‘’ሕዝብ ተማሯል እንባውን እንዲያብስለት የተቋቋመው የእንባ ጠባቂ ተቋምም ሰሚና አድማጭ አላገኘም ምን አገባችሁ እየተባልን የሥራ አስፈጻሚው መሳቂያ ሆነናል ሲሉ መናገራቸው በኢትዮጲያ ቴለቪዥን በድምጽና በምስል ቀርቧል።’’

ከኢትዮጲያ ቴለቪዥን ተውስዶ ሐገር ቤት በሚታተመው ሠንደቅ ጋዜጣ ላይ ጭምር የሰፈረው የወ/ሮ ፎዚያ አሚንና የሌሎች ባልስልጣናት አስተያየት በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት እንዳይካሄድ መደረጉን በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላም ሲሸጋገር ቆይቶ ዘግይቶና ይተላለፋል ባልተባለበት ቀን መተላለፉ ከሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ መረዳት ተችሏል።

የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕውሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አባይ ፀሐዬ የሕውሐት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ዶር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተመሳሳይ ችግሮች መኖራቸውን አስታውቀዋል። በተለይም የስኳርኮርፖሬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ የመንግስት ተቋማትን ለመቆጣጠር የሚደረገው እንቅስቃሴ አጥጋቢ አይደለም ብለዋል እነዚህ ተቋማት ግንዱን ትተው ቅርንጫፎቹ ላይ ይረባረባሉሲሉም ተችተዋል

 

Received on Fri Nov 16 2012 - 15:16:27 EST
Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2012
All rights reserved