በባድሜ ግንባር ኢሳትን ሲመለከቱ የተገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታስረው ተፈቱ
ESAT Daliy News Amsterdam Nov 22 2012 Ethiopia
http://www.youtube.com/watch?v=gauuAY_arnk <
http://www.youtube.com/watch?v=gauuAY_arnk&list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&feature=player_embedded> &list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&feature=player_embedded
ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
22.11.2012
ኢሳት ዜና:- ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ አንድ ባለማእረግ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደገለጸው በክበባቸው ውስጥ በናይልሳት ቻናል የኢሳትን ዝግጅት ሲከታተሉ የተገኙ በርካታ ወታደሮች ከ14 ቀናት እስር በሁዋላ በከባድ ማስጠንቀቂያ ተለቀዋል።
ወታደሮቹ የዲሻቸውን አቅጣጫ ወደ ናይል ሳይት ያዞሩት የውጭ ፊልሞችን ለመከታተል በማሰብ እንጅ ኢሳት የሚባል ጣቢያ መኖሩን በማወቃቸው አለመሆኑን ለአለቆቻቸው ተናግረው መፈታታቸውን መኮንኑ ተናግሯል።
በሰራዊቱ ውስጥ ያለው አጠቃላይ ስሜት ጥሩ አይደለም የሚለው መኮንኑ ከኢኮኖሚ ችግር ባለፈ ከፍተኛ የሆነ የአስተዳዳር በደልና በዘር መከፋፈል ይታያል ብሎአል።
አብዛኛው የሰራዊት አባላት መከላከያን የተቀላቀሉት በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ቢሆንም ፣ በተለይ ከኮሎኔልነት በታች ማእረግ ያላቸው ወታደሮች ከተራው ወታደር ያላነሰ ገቢና ተደማጭነት እንደሌላቸው ተናግሯል።
በሰራዊቱ ውስጥ ጥሩ የሚባል መንፈስ እንደሌለ የሚገልጸው መኮንኑ ፣ በተለይ በአሁኑ ሰአት ያለው ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ መሆኑን አክሏል።
ከኮሎኔልነት በላይ ማእረግ ያላቸው አዛዦች ከበታቾቻቸው ጋር ሲነጻጻሩ በተሻለ የአኗኗር ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተራው ወታደር ሳይቀር እንደሚያውቅ መኮንኑ ተናግሯል
በመጨረሻም የመከላከያ አዛዦች በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቤቶችን ሰርተው እንደሚያከራዩ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ይቀርባል ሰራዊቱ ይህን ያውቃል ወይ? ተብሎ ለተጠየቀው፣ ሰራዊቱ ሁሉንም ነገር ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ተናግሯል።
ኢሳት ከወራት በፊት የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሰርተው የሚያከራዩዋቸውን ቤቶች እና የቤቶችን ዋጋ ይፋ አድርጎ ነበር።
በወረዳ 17፣ በቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ጄኔራል ወዲ አሸብር የሚያሰሩት የንግድ ድርጅት፣ 55 ሚሊዮን የሚፈጅ ሲሆን ፣ ኮሎኔል ታደሰ የሚያሰሩት እና ካልዲስ ኮፊ የተከራየው ደግሞ 12 ሚሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበታል። ከዚሁ ህንጻ ጀርባ ጄነራል ዮሀንስ የሚያሰሩት ህንጻ ደግሞ 45 ሚሊዮን ብር ይወጣበታል። ጄነራል ባጫ ደበሌ ለኤቢሲ ካር ሬንት ያከራዩት ቤት ደግሞ 9 ሚሊዮን ወጪ አውጥቷል።
Received on Thu Nov 22 2012 - 22:31:33 EST