Basic

Mereja.com: የህወሓት መንግስት ‹‹በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊሲ ልከተል ነው›› አለ

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Tuesday, 19 September 2017

BBN : የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መንግስት ኤርትራን በተመለከተ አዲስ ፖሊሲ ሊከተል መሆኑን ገለጸ፡፡ ህወሓት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል በሰጠው መግለጫ፣ ኤርትራን በተመለከተ አዲስ ፖሊሲ ለመከተል መወሰኑን ቢገልጽም፣ ስለ ፖሊሲው ምንነት ግን ከመናገር ተቆጥቧል፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታት የኤርትራን መንግስት በመውቀስ እና በማብጠልጠል ላይ ተጠምዶ የቆየው የህወሓት መንግስት፣ አሁን የፖሊሲ ለውጥ ለማድረግ የፈለገበትን ምክንያት በግልጽ ለመናገር አልደፈረም፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው መግለጫ ‹‹የኤርትራ መንግስት በአሁን ሰዓት ለኢትዮጵያ ስጋት አይደለም፡፡›› ተብሏል፡፡ በህወሓት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ይበል እንጂ፣ አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚካሔዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች የኤርትራን መንግስት ከመወንጀል ወደኋላ ያለበት ጊዜ እንደሌለ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሔዱ ማንኛውም ዓይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በኤርትራ መንግስት ላይ በማላከክ የሚታወቀው የህወሓቱ መንግስት፣ መብታቸውን ለመጠየቅ አደባባይ የሚወጡ ኢትዮጵያውያንን ‹‹የሻዕቢያ ተላላኪ፤ የኤርትራ መንግስት ቅጥረኞች፡፡›› እያለ መወንጀሉን ሳይተው፣ የኤርትራ መንግስት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል መባሉ ተራ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡

ባለፉት ዓመታት የተቃውሞ ፖለቲካ አራማጅ የሆኑ አያሌ ኢትዮጵያውያን ‹‹የሻዕቢያ ተላላኪ፡፡›› ተብለው በአሻባሪነት እየተፈረጁ ወህኒ መውረዳቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ድርጊት በአሁን ሰዓት ተጠናክሮ ቀጥሎም የህወሓትን መንግስት የሚቃወሙ በርካታ ሰዎች፣ በኤርትራ መንግስት ተላላኪነት ተፈርጀው እና ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ይገኛሉ፡፡ ይሔ ሁሉ ሁኔታ ባልተቀረፈበት በዚህ ሰዓት፣ ህወሓት ‹‹የኤርትራ መንግስት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡›› የሚል መግለጫ መስጠቱ እንዳሳቃቸው ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ስጋት ካልሆነባቸው ታድያ ለምን በተደጋጋሚ ስሙን እየጠሩ ንጹኃንን ያስራሉ?›› ሲሉም ታዛቢዎቹ ጥያቄ አከል አስተያየት ይሰነዝራሉ፡፡

  1.  

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events