Basic

ዶ/ር ወርቅነህና አቶ ለማ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በአስመራ ተወያዩ

Posted by: Ghezae Hagos

Date: Tuesday, 07 August 2018

ዶ/ር ወርቅነህና አቶ ለማ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በአስመራ ተወያዩ

ዶ/ር ወርቅነህና አቶ ለማ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በአስመራ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በኤርትራ ከሚገኙት የኦነግ አመራሮች ጋር ለመደራደር ወደ አስመራ ባቀኑበት ወቅት ነው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር የተገናኙት።

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና አቶ ለማ መገርሳ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በነበራቸው ቆይታም በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

እንዲሁም በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈረመው የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት ተፈፃሚ የሚደረግበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በኤርትራ አስመራ የሚከፈተውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳይሌን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ተሳትፈዋል።

work_isu_1.jpg

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሀምሌ 1 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ቀናት በኤርትራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነትን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መፈራረማቸው ይታወሳል። 

በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት በይፋ ማስቆምና ወደ አዲስ የግንኙነትና ወዳጅነት ምዕራፍ ለመሸጋገር ስምምነት ፈጽመዋል።

በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራትም ሁለቱ መሪዎች በፊርማቸው አረጋግጠዋል።

የአየርና የየብስ ትራንስፖርትን ማስጀመር፣ የተቋረጠውን የመደበኛ ስልክ አገልግሎት እንዲሁም የንግድ ግንኙነታቸውን ማስጀመርም የመሪዎቹ የስምምነት ፊርማ አካል ነው።

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማስጀመር በመስኩ ያቋረጡትን እንቅስቃሴ ለማስቀጠልም ተስማምተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአስመራ የኤርትራ ኤምባሲ ደግሞ በአዲስ አበባ አበባ የሚከፈት ይሆናል።

ሃገራቱ በአልጀርሱ ስምምነት የገቧቸው የድንበር ስምምነቶች ገቢራዊ እንዲሆኑና፥ ሁለቱ ሃገራት በቀጠናው ሰላም፣ ልማትና ትብብርን ለማምጣት በጋራ እንደሚሰሩም በስምምነታቸው ወቅት ገልጸዋል።

ስምምነቱን ተከትሎም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ተቋርጦ የነበረው የስክል አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን፥ የአየር ትራንስፖርትም ዳግም ጀምሯል። 

እንዲሁም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ ዳግም ተከፍቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ኤርትራ አዲስ አምባሳደር ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የሾመች ሲሆን፥ ኢትዮጵያም አዲስ አምባሳደር ወደ ኤርትራ መመደቧ ይታወሳል።

 


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events