Basic

(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 15 August 2018

የአማራ ክልል ልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና

የአማራ ክልል ልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና።

ልዑኩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘገባ ያመላክታል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት አቋርጠውት የቆዩትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በቅርቡ መጀመራቸው ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በየሃገራቱ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የልማት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ኤርትራ በበኩሏ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በይፋ መርቃ ከፍታለች።

ከመሪዎቹ ጉብኝት ባለፈም በኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉም የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ በኩልም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወደ ኤርትራ በማቅናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸውም ይታወሳል።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events