Basic

(ኤፍ ቢ ሲ) የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Friday, 12 October 2018


የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ የሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በዛሬው እለት ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም፥ ለጁሴፔ ኮንቴ ሽኝትት እንዳደረጉላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ተወያይተዋል።

በወቅቱም ሃገራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና ለውጡን የሚመራውን መንግሥት አድንቀው ጣሊያን የለውጡን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረውን የጦርነት ሁኔታ በአዲስ የሰላምና የወዳጅነት ምዕራፍ መተካቱ በሳል እርምጃ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በሁለትዮሸና በባለብዙ ወገን መድረኮች ሁለቱ ሀገራት ያላቸው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም በውይይታቸው ወቅት ገልጸዋል።




7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events