Basic

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል

Posted by: Semere Asmelash

Date: Sunday, 14 October 2018

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል





አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።




ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ወደ ተግባር ከተሸጋገረ ጊዜ አንስቶ ጥልቀት እያገኘ በመጣው በሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግርዋል።

በተጨማሪም በንግድና ልዩ ልዩ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱም ነው ሀላፊው የተናገሩት።





ለሁለት አስርት ዓመታት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የቆዩት ሁለቱ ሀገራት፥ በወራት ውስጥ ግንኙነታቸውን አድሰዋል።

ሀገራቱ በጦርነት ምክንያት ተዘግቶ የነበረውን ድንበራቸውን ከመክፈት ጀምሮ የዓየርና የየብስ ትራንፖርትን ጀምረዋል።

በየዋና ከተሞቻቸውም ኤምባሲዎቻውን ከፍተው መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ጀምረዋል።

















EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events