Basic

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

Posted by: Semere Asmelash

Date: Saturday, 16 February 2019

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

On Feb 14, 2019

6:24

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል


አዲስ አበባ፣የካቲት 14፣2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ይገባል።

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ጉብኝት ለመጀመር በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የሚገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ቡድን ልዑኩ 55 አባላትን ያካተተ ሲሆን÷ እውቁ አርቲስት በረከት መንግስትአብ እንደሚገኝበትም ነው የተገለጸው፡፡

ይህ ልዑክ ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጋር አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የሁለቱ ሀገራትን የደም ትስስርና የማያቋርጥ ግንኙነት የሚያንፀባርቁ የባህል ሙዚቃዎችና ልዩልዩ ዝግጅቶችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጉብኝቱ አላማ የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑኩ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆያታ በተለያዩ ዝግጅቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም ልዑኩ የፊታችን የካቲት 9 ቀን በባህርዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ፣ የካቲት 12 በሀዋሳ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ነው የተገለጸው፡፡

በመጨረሻም የማጠቃለያ ዝግጅቱን የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም 25 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያቀርባል ነው የተባለው፡፡

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ኤርትራ የሚመለስ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ቡድንም ለተመሳሳይ ዓላማና ዝግጅት ከአንድ ወር በኋላ ወደ ኤትርራ አስመራ እንደሚጓዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

በባህላዊ የሙዚቃ ኮንሰርቱም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል ከየካቲት 3 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 32ኛ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን በመግለጽ÷ ኢትዮጵያም እንደ አስተናጋጅ ሀገር የሚጠበቅባትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣቷንና ከጉባኤው ማግኘት የሚጠበቅባትን ጥቅም ማግኘቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡

በስላባት ማናዬ




EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events