Basic

(ኢዜአ) ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 25 December 2019

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ


ኢዜአ፤ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር  አዲስ አበባ ውስጥ በእንጦጦና አካባቢው የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር በመሆን በእንጦጦ አካባቢ የሚገኘውን የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ በእንጦጦ አካባቢ የፕሮጀክቱ አካል ሆነው እየተካሔዱ ያሉ የመንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ጎብኝተዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን እንደመጡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል  ለዓመታት  ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነታቸውን እንደገና እንዲጀምሩ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትት ዶክተር አብይ በሐምሌ ወር 2010 ዓ.ም ወደ አሥመራ ተጉዘውም  በሁለቱ አገሮች መካከል  የነበረውን ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።

ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ዛሬ ረፋድ ላይ መምከራቸው ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ... - FBC

.ena.et/?p


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events