Basic

(አብመድ) "ከ50 ዓመታት በኋላ ጥምቀትን በጎንደር በድጋሜ ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።" በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Monday, 20 January 2020

"ከ50 ዓመታት በኋላ ጥምቀትን በጎንደር በድጋሜ ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።" በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ


የኤርትራ ልዑክ ጥምቀትን በጎንደር እየታደመ ነው። በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ የተመራ የኤርትራ ልዑክ ዛሬ ጠዋት ነው የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር የገባው። የከተማዋ ነዋሪዎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከአቀባበል ጀምሮ ላሳዩት አክብሮት አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተብሎ ይጠራ በነበረው በዛሬው ፋሲለደስ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነው ይሰሩ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በወጣትነት እድሜያቸው ጥምቀትን ከጎንደር ሕዝብ ጋር ያከብሩ እንደነበር አስታውሰው ከበርካታ ዓመታት በኋላ የዘንድሮውን ጥምቀት በመታደማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

በከተማዋ ይኖሩ የነበሩ፣ ልዩ ትዝታ ያላቸው ኤርትራውያን ታሪካዊቷን ጎንደር ከተማን የመመልከት እድል ሰፊ ሊሆን እንደሚገባም ነው አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ሀደራ ሀሳብ የሰጡት።

ሁለቱ ሀገራት ወደ ሰላማዊ ስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ አዎንታዊ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም በተለይ ለአብመድ ተናግረዋል።

ወደፊት የጦርነት ድምፅ የማይሰማበት ጊዜ እንዲመጣ፣ በሁለቱ ሀገራት መሪዎችና ባለስልጣናት የተጀመረው ግንኙነት ወደ ሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት ማደግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት።

ዘጋቢ:- ኃይሉ ማሞ


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events