Date: Monday, 04 May 2020
አዲስ አበባ (ኤፍ ቢ ሲ)የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።