Dehai News

Ethsat.com: የመምህራን የግምገማ ሪፖርት በኢሳት መተላለፉ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣ ፈጥሯል።መምህራኑ ዳግም ትሃድሶ እንዲያደርጉ የታዘዙበት ሰነድም እጃችን ገብቷል

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 09 March 2017

የመምህራን የግምገማ ሪፖርት በኢሳት መተላለፉ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣ ፈጥሯል።መምህራኑ ዳግም ትሃድሶ እንዲያደርጉ የታዘዙበት ሰነድም እጃችን ገብቷል

March 9, 2017

Watch these:

ESAT Daily News Amsterdam March 09,2017

https://www.youtube.com/watch?v=NycwiYeVBpM

ESAT DC Daily News Thur 09 Mar 2017

https://ethsat.com/2017/03/esat-dc-daily-news-thur-09-mar-2017/

 

የካቲት ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን አስደንጋጭ የተሃድሶ ግምገማ ሪፖርት በኢሳት መተላለፉን ተከትሎ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ኢህአዴግ፣ አሁን ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ዳግም ትሃድሶ እንዲያካሂዱ ቀጭን ትእዛዝ ተላልፏል። ዩኒቨርስቲዎችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ትሃድሷቸውን እንዲወጡ በታዘዙት መሰረት፣ ትምህርት ዘግተው የተሃድሶ ውይይታቸውን እያደረጉ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር በ25/06/2009 ዓም “ አስቸኳይ ዳግም ተሃድሶ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲያካሂዱ ስለመገልጽ” በሚል ርእስ በጻፈው ደብዳቤ፣ “የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል መምህራን የተሰጠውን ምላሽ እና በህዝቡ መካከል የተፈጠረው ምስል አሉታዊ ሁኖ በመገኘቱ ፤ ሁሉም የዩኒቨርስቲ መምህራን እና ተማሪዎች ከቀን 27-06-09 ጅምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ቢበዛ በስድስት ቀናት ውይይት “ እንዲያደርጉ አዟል። ደብዳቤው “ውይይቱ ሚስጢራዊነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የየቀን ውሎ ሪፖርት እንዲደርሰን” የሚል ትእዛዝ ያከለበት ሲሆን፣ በተለይ “አሉታዊ አመለካከት ያላቸው መምህራን ተለይተው በፖሊሲው ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ክትትል እንዲደረግባቸው ፣ በተጨማሪም በየዩኒቨርስቲው በተመደቡት የኢህአዴግ ፓርቲ አስተባባሪዎች ክትትል እንዲደረግባችው በጥብቅ እናሳስባለን” በማለት የካዳሚክ ጉዳዮች ሃላፊ ዶ/ር ዘሪሁን ከበደ ለ31 ዩኒቨርስቲዎች ደብዳቤውን ፈርመው ልከዋል።

አዲስ ለስልጠና የሚመደቡ መምህራንም ተሃድሶውን ካልወሰዱ መመረጥ እንደማይችሉ በደብዳቤው ላይ ተጠቅሷል።

ደብዳቤው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተሃድሶ በሚል የሚያዘጋጀው ስብሰባ፣ አገዛዙን የሚቃወሙትን ምሁራንን ለመለየት እና ጥቃት ለመሰንዘር እየተጠቀመበት እንደሆነ ቀደም ብሎ ሲሰጥ የነበረውን አስተያየት የሚያረጋግጥ ሆኗል። በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የህውሃት ሁለት ሁለት አስተባባሪዎች ፣ የብአዴን ፣ የኦህዴድ ና የደህዴን አንድ አንድ አስተባባሪዎች ተመድበው፣ ተማሪዎችን ተቃውሞ እንዳያነሱ ለማግባባት እየሞከሩ ነው። አንዳንድ ተማሪዎች “ስትመረቁ ስራ በቀጥታ የምታገኙት የኢህአዴግ አባል ስትሆኑ ብቻ ነው” እየተባለ እየተነገራቸው ነው። እነዚህ ቀስቃሽ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ 24 ስዓት እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።

ለኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ብቻ የተላከው የሚስጥር መረጃ ኢሳት እጅ ከገባ እና የህዝብ መነጋጋሪያ ከሆነ በሁዋላ ደግሞ፣ መምህራን፣ “ከሽርፍራፊ ሰከንድ ማባከን ጀምሮ ኪራይ ሰብሳቢነት ይታይብናል ፣ መንግስትን እና ማህበረሰቡን በድለናል” እያሉ እንዲናገሩ የሚደረግበት ስብሰባ በከፍተኛ አመራሩ መድረክ መሪነት እንደገና እንዲካሄድ ተወስኗል፡። በዚህ በተከታታይ በሚደረግ የድጋሜ ጥልቅ ተሃድሶ ኢህአዴጋዊ ዘጋቢ ፊልም በመስራት፣ በአሁኑ ስዓት የቦንብ ናዳ ያወረደውን የግምገማ ሰነድ እና የመምህራን አመለካከት ለመለወጥ መታቀዱን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል።

በዚህ አመት በጎንደር ፣ ደብረ ታቦር ፣ ወልድያ ፣ አክሱም ዩኒቨርስቲዎች አመፆች ተነስተው በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በድንገት ተካሄደ በተባለ ፍተሻም ቦንቦች ተገኝተዋል በሚል ጥርጣሬ የታሰሩ ተማሪወች እስካሁን አልተፈቱም፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማውን ለአራተኛ ቀናት አድርገው ውለዋል። ለመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሲደረግ ለመምህራን በመዘዘሉ “ መምህሩ ተንቋል” ያሉ የአማራ ክልል መምህራን የስራ ማቆም አድማውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ የደቡብ ክልል መምህራንም አድማውን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ናቸው።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸኛ ወረዳ የተጀመረውን የመምህራን አድማ ተከትሎ፣ ያለፈው ማክሰኞ በርካታ መምህራን ታስረው በእስር ቤት ድብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ዛሬ ሃሙስ ደግሞ እንደገና ዳልፎር ከሚባል ትምህርት ቤት 10 መምህራን ተይዘው ታስረዋል። የከተማዋ ፖሊሶች ወደ መምህራኑ ቤት በመሄድ፣ መምህራኑን እያወጡ በመደብደብ ወደ እስር ቤት መውሰዳቸውን የገለጹት የአይን እማኖች፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ መምህራኑ ከእስር አልተፈቱም። በሸበል በረንታ፣ ቡብኝ፣ ደባይ ጥላት ግን በመሳሰሉት ቦታዎች ተመሳሳይ አድማ የተደረጉ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት የታሰሩት መምህራን ተፈትተዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ መካነሰላምና ወግድ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ መምህራን አድማውን አድርገዋል። በዋግ ህምራ ዳህና ወረዳ 5 መምህራን አድማ አነሳስታችሁዋል በሚል ታስረዋል። በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በእስቴ ወረዳ የመካነየሱስ ትምህርት ቤ/ት መምህራንም እንዲሁ አድማ እያደረጉ ነው።

አድማው በአብዛኛው የአማራ ክልል እየተካሄደ ሲሆን፣ የደቡብ ክልል መምህራንም እንዲሁ አድማውን ለማድረግ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው። በጋሞጎፋ ዞን በዲታ ደራማሎ ወረዳ ደግሞ የጋሞኛ ቋንቋ መምህራን የተባሉ ከ8ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ተምረው ውጤት ያላመጡትን ከ300 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን፣ ከትምህርት ፖሊሲው ውጭ በድጎማ መምህርነት በ400 ብር ቀጥረው ለአመታት እንዲሰሩ ከተደረገ በሁዋላ፣ መምህራኑ “ለእኛስ ማስተካከያ አይደረግልንም?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ለእናንተ አይስተካካልም፣ ብትፈልጉ ልቀቁ” በመባላቸው፣ አድማውን ከሌሎች የክልሉ መምህራን ጋር በመሆን ፊት ሆነው ለመምራት ተሰልፈው እንደሚገኙ ለክልሉ ወኪላችን ገልጸዋል።

*******************************************************************************

የወልቃይት ጉዳይ የአማራ ክልልንም ሆነ ብአዴንን አያገባውም ሲሉ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

March 9, 2017

የካቲት ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከክልሉ ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ “ስለወልቃይት ጉዳይ የሚያገባው የትግራይ ክልልና የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንጅ የአማራ ክልል አይደለም” ብለዋል።

“ በወልቃይት፣ በራያ እና ሌሎችም አካባቢዎች፣የትግራይ ክልል ከአማራ ክልል መሬት እየወሰደ ነው፣ ዳሸን ተራራና ላሊበላ ሳይቀር የእኔ ነው እያለ ነው፤ በየጊዜውም በትግራይ መገናኛ ብዙሃን የታጠቁ ሰዎች እየቀረቡ ሽለላ ያሰማሉ፣ በአማራ ክልል በተቃራኒው አገራዊ ሙዚቃ እንኳን እንዳናሰማ እንከለካለን” የሚሉና ሌሎችንም በርካታ ጥያቄዎችን በጽሁፍ ያቀረቡት ጋዜጠኞች፣ ከአቶ ንጉሱ ጥላሁን አጥጋቢ መልስ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ። አቶ ንገሱ “የወልቃይት ህዝብ ተቃውሞ ባሰማ የባህርዳር ፣ የጎንደር ፣ የዳንግላ፣ የመራዊ ህዝብ ምን አገባው? ድንበር ላይ በተነሳ ጥያቄ፣ ማሃሉ ለምን ይቃጠላል?” የሚል ህዝብን የሚከፋፍልና የአንዱ አካባቢ ህዝብ ለሌላው እንደማይመለከተው የሚያሳይ መልስ ሰጥተዋል። “ የቅማንት ጥያቄ በአማራ ክልል በቅድሚያ እንደሚታየው፣ የቁጫ ጥያቄ በደቡብ ክልል እንደሚታየው ሁሉ፣ የወልቃይት ጥያቄም በትግራይ ክልል መንግስት መታየት ሲገባው፣ ጎንደርን የሚያቃጥልበት፣ ባህርዳርን የሚያቃጥልበት፣ ደብረታቦርን የሚያቃጥልበት፣ አማራ ክልልን የሚያቃጥልበት አንዳች ምክንያት የለም” በማለት የብአዴንን አቋም ግልጽ አድርገዋል።


7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events