Dehai News

Satenaw.com: ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር– ክፍል 1ና 2

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Saturday, 01 July 2017

/ጄነራል ጻድቃን ህወሃት ኤርትራ እና ቀይ ባህርክፍል 1ና 2

ጄነራል ጻድቃን፣ የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ እና የፓለቲካ ችግሮች

 

በነጻነት ቡልቶ

https://1.bp.blogspot.com/-psX91OySq8I/U8w6ruifSTI/AAAAAAAAGTM/NR-0AN6p1K4/s1600/Ethiopian+General+Tsadkan+Gebretensae.jpg
 

***ኣነ ስጋብ ሕጂ ኣብ ታሪኽ ካብ ዘምበብኩዎ ብዓመጽቲ ስርዓታታት ኢትዮጵያ ደሓር ድማ ብናይ ሎሚ ዓሌታውን ኣረሜናውን ስርዓት ወያነ ትግራይን መሳፍንቲ ናይ ኲናት መራሕቱን፣ ኣብ ልዕሊ ኤርትራ ዘካየድዎ ወራር ሌተናይ ጻድቃን ገብረትንሳኤ ንሱ ዝእዝዞም ላዕለዎትን ማእከሎትን ናይ ሰራዊት ኢትዮጵያ ሓለፍቲ ኣብ ኣደራሽ ኣኪቡ በቲ ኣብ እግሪ-መኸል ኤርትራ መጋቢት 1999 ዓም ፈረንጂ ዝተገብረ ከቢድን ኣዕናውን ኲናት ክዝቲ ዝሓሰቦ ብስዕረቱን ፍሽለቱን ግን ኤይ ኤይ……ኢሉ ዝበኸየን/ዘላቐሰን ናይ መጀመርያ እንኮ ጀነራል እዩ።

***ብርሃነ ሃብተማርያም

 

በግሪክ አቴናና በስፓርታ መካከል የተካሄደውን የጦርነት ታሪክና ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ ስትራቴጃካዊ ጽንሰ ሃሳቦች በማፍለቅ ከሚደነቀው ጥንታዊው የታሪክ ጸሃፊ የቱስዳይስ The Peloponnesian war ጀምሮ እስከ የጀርመኑ ካርል ቮን ክልሽዊትዝ On War የባህር ሃይል ስትራቲጂ አባት አልፌሬድ ማሃን The influence of Sea Power Upon History ከዘመን ተሻጋሪ የስትራቴጂ አስተምሮዎች ፈላስፋ ቻይናዊው ከሰን The Art of War አንስቶ እሰከ ሉትዋርክ፣ ኮሊንስ የመሳሰሉ የዘመናችን የስትራቴጂና የደህንነት ጥናቶች ታላላቅ ተመራማሪዎችና ምሁራን የጻፏቸውንና ያፈለቁዋቸውን የስትራቴጂ ጽንሰ ሃስቦችና ቀመሮች በጥልቀት ማጥናትና ማወቅ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው፡፡ የሴኪዩሪቲና የስትራቴጂ እውቀቶችን ባካበቱ ምሁራንና ተመራማሪዎች የሚጻፉ የአብይ ስትራቴጂ (Grand strategy) ንድፈ ሃሳቦችና ጽንሰ ሃሳቦች፣ ከነዚህ የሚመነጩ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ቀመሮችን ተመርኩዞ የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲዎችን መንደፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተጋረጡባት ድርብርብ የፖለቲካ ችግሮችና ከችግሮቹም የሚመነጩትን ዘርፈ ብዙ የደህንነት አደጋዎችን ለመከላከል የማይናቅ ድርሻ አላቸው። በእነዚህም ዙሪያ ጥልቀት ያላቸው ጥናቶችን ማድረጉ አስፈላጊ ነው። እነዚህንም የሚያስፈጽሙ አካላት መኖርና መጠናከር ለኢትዮጵያም ሆነ ለማንም ሀገር አስፈላጊ ከሆኑ ተቋማት ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጡ መሆናቸው አይካድም። ከዚህ አኳያ ጄነራል ጻድቃን በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎችና ተቋማት ለአንድ ሃገር የሚበጁ እንደሆኑ ወደ አደባባይ ጉዳዩን ማቅረባቸው ያስመሰግናቸዋል።

 

ነገር ግን በዋነኝነት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ስርአት መሪዎች ባህሪ የፖለቲካ ታሪካቸው (track record) የሚከተሉት ኣካሄድና የፓለቲካ ፍላጎት በሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ቀዳሚና ወሳኝ (Decisive) ድርሻ እንዳላቸው ክርክር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። ይህንን ቀላል ዕውነት መረዳት የችግሮቻችንን መሰረት ለማወቅ አውቆም በቀዳሚነት የሚያስፈልገው ያለፈው 26 አመት ህወሃት የዘረጋውን የፓለቲካ ስርአትና ተከትሎት የመጣውን ግዙፍ የደህንነት አደጋዎች ለመገንዘብ ይረዳናል። ይህን አደጋ ለመቀልበስ ደግሞ ቁርጠኝነትና የፓለቲካ ወኔ (Political will) መኖር ዋናው ቁልፍ ነው። ይህም በመሆኑ ነው የፓሊሲዎች ቈንጮ የሆነውን የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ በባለቤትነት፣ በአስፈጻሚነትና በኣስተግባሪነት አሁን ላለው የሀገሪቱ የደህንነት ስጋት ዋና ቀፍቃፊ ምንጭ ለሆነው የሕወሃት አመራር መስጠት ውሻን ሉካንዳ ቤት እንዲጠብቅ ከማድረግ ይቆጠራል ብዬ የምከራከረው። የብሄራዊ ደህንነት አደጋዎች አመንጪና አሽከርካሪ (driver) የሆነውን አካል የዚህ ፖሊሲ ባለቤትና አስፈጻሚ ማድረጉ ስርአቱን ትንሽ ጠጋግኖ ለማስቀጠል ይረዳ እንደሆን እንጂ በዘለቄታው የኢትዮጵያን የደህንነትና ተያያዥነት ያላቸውን ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ ችግሮች ማስወገድ አይቻልም። እንዳውም በተቃራኒው እነዚህ ዘርፈ ብዙ የሀገሪቱ የፓለቲካ ችግሮች ተወሳስበው መቀጠላቸውና ሀገሪቱንም ሆነ የአፍሪካ ቀንድን ለከፋ ትርምስና የደህንነት ኣደጋ ማጋለጣቸው አይቀሬ ነው።.........................

 

.................ምንባቡ ቀጽሎ

ብርሃነ ሃብተማርያም


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events