Dehai News

Satenaw.com: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትን ትንሽ እንቃኘዉ።

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 10 August 2017

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትን ትንሽ እንቃኘዉ። 

– ሎኡል አለሜ

ሳተናው
By ሳተናው August 10, 2017 19:17

 

በኤርትራ የተጀመረዉን ጦርነት እነ መለስ ዜናዊ በቶሎ ለመመከት አልቻሉም ነበር በዚያ ትርጉም አልባ ጦርነ ላይ በአመራር ላይ የነበሩት ሰአረ መኮንን፣ ሳሞራ የኑስ፣ ዮሐንስ ገብረመስቀል፣ ታደሰ ወረድ፣ ዋና አዛዥ አብረሐ ወ/ማርያም፣ እና ብርሃኔ ነጋሽ ሲሆኑ የመካከለኛ እዝ (The Central Command leaders) መለስ ዜናዊ፣ ሲየ አብረሃ፣ ተወልደ ወ/ማርያም፣ አለምሰገድ ገ/ሚካኤል፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ ኪንፈ ገ/መድህን ነበሩ

በኤርትራ በቅጥጥር ስር ዉለዉ በአየርና በከባድ መሳሪያ ሊደረመሱ የማይቻሉ ምሽጎች የተሰሩባቸዉ ቦታዎች ቡሬ፣ዛላምበሳ፣ ጾረናና፣ባድሜ ናቸዉ ለምሳሌ ከምጽዋ እስከ ቡሬ ግንባር ያለዉ እርቀት 70 ኪ/ሜ ሲሆን ኤርትራ በተለይም 19ኛዉና 39ናዉ ክ/ጦር በቡሬ ግንባር 70ባዉን ኪሎ/ሜ ወደ ፊት መጥቶ የኢትዮጵያ መከላከያ ካለበት 1. ኪ/ሜ እርቀት ላይ አይበገሬዉን ምሽግ በፌሮ ብረትና በኮንክሪት ገንብቷል ይህ ማለት ብሁሉም የጦር ግንባሮች የተሰራ ሲሆን የተለያየ ሐገር የጦርና የፖለቲካ ጠበብቶች የማይደፈር በማለት አሞካሹት ምሽጉ እዉነትም አይደሬ ነበር ።

የመካከለኛዉ የኢትዮያ መንግስት ጦርነቱን ለመጀመር የወታደር እጥረት ስላጋጠመዉ በአጠቃላይ ሐገሪቱ የክተት አዋጅ አወጣ የክተት አዋጁ በፍቃደኝነት ህዝቡን መጥራት አንዱ መንገድ ሲሆን በዚያ መንገድ አጥጋቢ ዉጤት ካልተገኘ የወታደሩን ደሞዝ 600 ብር በማዉጣት ጥሪ ማድረግ ከነዚህ መንገዶች ዉጭ አማራጭ ከጠፋ ማስገደድ የመጨረሻዉ ዉስኔ ነበር ነገር ግን ህወሃታዊያኑ ለአልባሌዉ ጦርነት ብዙም ሳይደክሙ ሐገርህ ተደፈረች የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ዉትድራናዉን አሜን ብለዉ በመቀበል ወደ ማሰልጠኛ ገቡ ህወሃት አንድ ሌላ ችግር ገጠመዉ ይህዉም ( ትግራይ ) የትግራይ ህዝብ ዉትድርናዉን አልቀበልም ጦርነት ሰልችቶናል አለ በተለያየ መንገድ ቢመከርም አሻፈረን በማለቱ ማእከላዊ መንግስቱ በትግራይና በዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ግዳጅ በማዉጣት ወጣቶችን ማሳደዱን ተያያዙት ልጅ ከጠፋ እናት ትጠየቅ ጀመረች። ወይኖች ይህን ያደረጉበት ምክንያት የሐይል መጠኑ እና የአዛዥ ታዛዥ ጉልበትን በትግራይ ህዝብ ለመሙላት እንጂ የትግራይን ትዉልድ በጦርነት ለመማገድ አልነበረም በመሆኑም ከአራት ወራት ወታደራዊ ስልጠና በሗላ የትግራይ ልጆች ተመረጡ የትምህርት ደረጃቸዉ ከፍ ያሉት ወደ አዛዥነት ተወሰዱ የትምህርት ደረጃቸዉ ዝቅ ያሉት ኦፕሬተርና የተለያየ ቦታ ተሰጣቸዉ ጥቂቶች ከሰራዊቱ ጋር የጀርባ ሐይል ሆነዉ ኤርትራ ገንብታ ወደ ተቀመችበት ምሽግ እርሱም ወደ ሞት መንደር ገሰገሱ።

ታደሰ ወረደ የቡሬ ግንባር አዛዥ ተደርጎ ቡሬን ደምስሶ አሰብንና ምጽዋን በቁጥጥር ስር የማዋል ጥእዛዝ ተቀበለ አብረሃ ወ/ገብረል ጾረና ግንባርን ብርሃኔ ነጋሽ ዛላምበሳ ግንባርን በበላይ አዛዥነት ሲረከቡ ተጠሪነታቸዉ ለጻድቃን እንዲሆን ተደረጉ ሳእረ መኮንን፣ ዮሃንስ ገ/መስቀል እና አበበ ታደሰ ባድሜ ግንባርን በአዛዥነት ሲረከቡ ሳሞራ የበላይ ተቆጣጣሪ ነበር።

ጥቃቱ በሁለት አቅጣጫ እንዲጠላለፍ የተደረገ ሲሆን ዋና አላማዉ ኤርትራን መቆጣጠር ነበር። ይህን መሰል የአዛዥ ታዛዥ ቡድድን ሲካሄድ ስለ ባለግርማ ሞገሶቹ ምሽጎች የሚያወራ አልነበረም ብቻ የ23ተኛ ክ/ጦ አዛዥ የነበረዉ በርሄ ገ/ማርያም ብዙ ጥያቄዎችን ቢያነሳም የሚሰማዉ አልነበረም በመካከለኛዉ መንግስት የወታደራዊ ስልት ግን ምሽጎቹን ለመደምሰስ የታቀደዉ ከትግራይ ብሔር ዉጭ በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች የሰዉ ሐይል ነበር።


ጦርነቱ ተጀመረ ባድሜ የመጀመሪያ ጥቃት ነበረች በዚያም የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ምሽጉ ገሰገሱ የመጀመሪያዉ ዙር በሙሉ ወደመ በተጨማሪ በጻድቃን ትእዛዝ ሁለት ክ/ጦር ባድሜን አጠቃ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ረገፉ ከምሽጉ መስኮቶች የሚወረወሩት የጥይት ሐሮሮች በሏቸዉ ጻድቃን ባድሜን በመተዉ ወደ ጾረና ግንባር እንዲዛወሩ ጥእዛዝ ሰጠ።


ትልቁ 20ኛዉ ክ/ጦር ባለ በሌለ የሰዉ ሐይል ገሰገሰ ኢትዮጵያዊያኑ በጀግንነት እየበረሩ ወደ ምሽጉ ይሮጣሉ ይረግፋሉ ብዙ ብዙ ደም ብዙ ብዙ ሲቃ ነገር ግን ወታደሩ ከነበረዉ የሰዉ ሐይል የተነሳ ወደ ምሽጎቹ መድረስ ተቻለ ምሽጎቹ ዉስጥ እየዘለሉ በምግባት ማጥቃት ቻሉ ሶረና በደም ተሸነፈች።


ጻድቃን ከአንድ ሳምንት እረፍት በኍላ ስብሰባ ጠራ በስብሰባዉ ላይ ስለ ሽንፈታቸዉ በግልጽ ተናገረ ብዙ ብዙ ዉጊያዎች ላይ ተሳትፌያለዉ እንደዚህ ግን የተዋረድንበት ዉጊያ የለም ሲል ተናገረ።


ከዚያ በተለያየ ወቅትና ግዜ የተለያዩ ምክክሮችን በማድረግ በድጋሚ ወደ ባድሜ ጥቃት መፈጸም ተጀመረ ዋነኛው አላማ ባድሜን በደንብ ስናጠቃ ሻቢያ ከሌሎች ግንባሮች ስለሚጨምር የተመናመኑትን ለማትቃት ይቻላል የሚል ነበር በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር ሐይል ጀቶች ምሾጎቹ ላይ ያደረሱት ጥቃት ዉጤት አልባ ነበሩ በመሆኑም ምሽጎቹ የሚሰበሩት በኢትዮጵያዊያን ወጣት ልጆች ብቻ ነበር።


ባድሜ ላይ በተከፈተዉ ከፍተኛ ጦርነት ይህ የማይባል ደም ፈሰሰ በዚያ ወቅት የቡሬ ግንባርን ማጥቃት ተጀመረ የቡሬ ግንባር ልክ እንደ ሌሎቹ ግንባሮች ጥይት ማብረጃ ተላከለት ወጣቶች ካካካካካካካካካካካ የጥይቱን ሐሩር እየጠጡ እየወደቀኡ እሬሳ እየዘለሉ ወደ ፊት ገሰገሱ የኤርትራ ጦር ድንገተኝ ትእዛዝ ተሰጠዉ በጾረና በኩል እና በዛላምበሳ በኩል የዘለቀዉ የኢትዮጵያ ወጣት ወደ አዲቋላህ በማምራት ጋሽባርክን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ላይ ሳሉ የቡሬ ግንባር ወደ ኍላ እንዲያፈገፍግ ታዘዘ በትእዛዙ መሰረት 37 ኪ/ሜ ርቀት ተመልሰዉ መሸጉ የኢትዮጵያ ጦር እየገሰገሰ መጣ ፈጽሞ አሰብን በቁጥጥር ስር ለማድረግ እንደዚህ ያለ አጋጣሚ አይገኝም ነበር ነገር ግን ከ37 ኪ/ሜ ላይ የሻቢያ ጦር መመሸጉ አልታወቀም ነበር ያ ለሻቢያ ጥሩ አጋጣሚ ነበር ወጣቱን ወደ አሰብ ከመድረስ ገዱት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ በሌላ በአዲ ቋላህ በኩል የኢትዮጵያ ወጣቶች እየገሰገሱ ሳለ ለ ችግር ተፈጠረ ዉጩ የተባለ የሻቢያ ጄኔራል ድንገት ጠረማምሶ ወደ ትግራይ ገሰገሰ ከኤርትራ መሐከላዊ መንግስት ከስብሀት ኤፍሬምና ከኢሳያስ አፎቂ የተሰጠዉን ጥእዛዝ ሊሰማ አልፈለገም ዝም ሎ ትግራይ ተመመ።


በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ የኢትዮጵያ ጦር እንዲያፈገፍግ ጥእዛዝ ተሰጠዉ በተመሳሳዩ የኤርትራ ሰትም ከትግራይ እንዲመለስ ጠንካራ መመሪያ ተላለፈለት ይህ ሁኔታ እስከዛሬ ያልተፈታ ህልም ነዉ። ኢትዮጵያዊያን በተለይም ከተለያየ ክፍላተ ሐገር ከተለያየ ብሔር የተዉጣጡ ወጣቶች አለቁ አለምን ባስደነገጠ መልኩ 70 ወጣቶች በዚያ ከንቱ ጦርነት ረገፉ። ጦርነቱ ትግራይን ለማዳን ወይስ እትዮጵያን ለማዳን የተደረገ እንደነ ማንም አያዉቅም ግን ደም እደዉሃ በከንቱ ፈሰሰ።

Dm eri tv subscribe

ERi-TV, Eritrea: Ethiopia Welcomes President Isaias Afwerki, July 14, 2018 - Part 1

Hdri Media Books on Amazon.com
visit hdrimedia.com